ሰላም ሰዎች በቁም ነገር መሀል ማሾፍ ማላገጥ መሳቅ ባህሪዬ ሆኖ ተጠናወተኝ አልስቅም ብል ራሱ ሳቄ ያመልጠኛል...በቃ በወሬ መሀል ቀልድ ፌዝ ጣል ካላደረኩ ይደብረኛል ደስ አይለኝም ...በዚህ ምክንያት አይደለም ጓደኞቼ እህቴ ራሱ አታወራኝም...ተሻሽያለሁ አላሾፍም ቁምነገር ላወራሽ ነው ብዬ አወራትና መሀል ላይ አምልጦኝ ወይ ቀልዳለሁ ወይ እስቃለሁ..እና ብዙ ጊዜ ለመሻሻል ሞከርኩ ግን አልቻልኩም በቃ በፌዘኝነቴ ሰው እያሸሸሁኝ ነው በዚህ ሁኔታዬ አድጎብኝ ወደፊት የሀገር መሪ ብሆን ስብሰባ መሀል ንግግር መሀል ላላግጥ ይሆንን ብዬ ሰጋለሁ ...እንዴት ነው በአንድጊዜ ይሄን የተጠናወተኝን የቀልድ ፌዝ ሳቅ አባዜ ሊያሻሽልልኝ የሚችል የጠቀማቹ ፅሁፍም ወይ ትምህርትም ሊሆን ይችላል ሀሳባችሁን አጋሩኝ..አመሰግናለሁ ።
May 11, 2025ኧረ እውነትሽን ነው አሁን እራሱ እኮ እያፌዝሽ ነው የሀገር መሪ…🙄 እሺ ግን ለማንኛውም ቁም ነገር የሆኑ ነገሮች ላይ አተኩሪ አብረሻቸው የምትውይው ሰዎችም effect ሊሆን ይችላል የሚያፌዙ ከሆነ አንቺም ያው... እንደ ሎሚ በሚኮመጥጥ ጊዜ ማፌዝ ግን ከባድ ነው።
May 11, 2025