የመፀሐፍ ቅዱስ ግጭቶች 3) እየሱስ ስለተሰቀለበት ቀን የዮሐንስ ወንጌል 19:31- "አይሁድም የማዘጋጀት ቀን ስለ ሆነ ያ ሰንበት ትልቅ ነበረና ሥጋቸው በሰንበት በመስቀል ላይ እንዳይኖር፥ ጭናቸውን ሰብረው እንዲያወርዱአቸው ጲላጦስን ለመኑት" ይላል እዚህ ጋር: ትልቅ ሰንበት የሚባለው የአይሁድ ፋሲካ የመጀመሪያ ቀን ሲሆን (በዓሉ ሳምንት ይቆያል) ስያሜውን ያገኘው እንደ ተለመደው ሰንበት በዕረፍት ስለሚያሳልፉት ነው። ነገርግን ይህ ትልቅ ሰንበት በየትኛውም ቀን ሊያርፍ ይችላል። በዚህ ቀን እርሾ የሌለው ዳቦ ስለሚመገቡ የቂጣም በዓል ይባላል። የማዘጋጀት ቀን ስራ ከማይሰሩበት ቀን በፊት ያለ ቀን ነው። ስለዚህ: ዮሐንስ እየሱስ የሞተበትን ቀን ከፋሲካ በዓል በፊት ያደርገዋል ጥያቄ 1) የመጨረሻው እራት ለማቴዎስ፣ ማርቆስ እና ሉቃስ የበዓሉ እለት ለዮሐንስ ግን ከበዓሉ በፊት ነው። ይታረቃሉ? 2) ስቅለቱ ለሦሥቱ ከበዓሉ ማግስት ሲሆን ለዮሐንስ በማዘጋጀት ቀን ከበዓሉ በፊት ነው። ይሄስ? 3) ወንጌሎቹ መሐል ያለው እንዲህ ያለ መቃረን ምንጫቸው አንድ እንዳልሆነ አያሳይም? 4) ይሄስ ከሆነ ለምሣሌ ስቅለቱ ላይ የምናገኘውን የተረጋጋ እና እየሆነ ባለው ተመሮ "ለምን ተለየኸኝ" ወይ ደም ያላበውን እየሱስ እንደ አንድ መመልከት ትክክል ነው? 5) ምንጫቸውስ አንድ ነው ካልን ግልፅ የሆነ አለመገጣጠማቸው እንዴት ይታረቃል?
May 11, 2025mndnw yawerahew.... kidame le ayhud senbet nw... friday dmo ye mezegajet ken nw... kidame ken lay mnm slemayseru arb hulunm chersew mader neberebachew...complex atargew
May 11, 2025