የመፀሐፍ ቅዱስ ግጭቶች 2) እየሱስ ከትንሣኤ በኋላ ለደቀመዝሙሮቹ ስለተገለጠበት ቦታ የማቴዎስ ወንጌል በምዕራፍ 28 ከቁጥር 16-20፣ የሉቃስ ወንጌል በምዕራፍ 24 ከቁጥር 36-53 እና የሐዋርያት ሥራ በምዕራፍ 1 ቁጥር 2-9 እየሱስ በሦሥተኛው ቀን ለአሥራአንዱ ሐዋርያት የት እንደተገለጸ እና ስላስተላለፈላቸው መልዕክት ይተርካሉ። ጥያቄ ገሊላ ወይስ እየሩሣሌም? የት ነው ለመጀመሪያ ጊዜ እየሱስን ያዩት? እሱ በሁለቱም ቦታ መታየት ቢችል እነሱ ሁለት ቦታ መገኘት ይችላሉ? የሐዋርያት ሥራ ጭራሽ ከእየሩሣሌም እንዳልወጡ ይናገራር ሉቃስ እዛው እንዳዩት ይነግረናል (የሐዋርያት ሥራ እና የሉቃስ ወንጌል አንድ ፀሐፊ እንያላቸው ይታመናል) ታዲያ ማቴዎስ ተሳስቷል? በመጨረሻም በተለያየ ጊዜ የተፃፉ፣ ከሚተርኩት ድርጊት በ50 እና 60 አመት የሚርቁን ፅሑፎች ስለአንድ ነገር የተለያየ ዘገባ ሲያቀርቡ አንዱን የሌላው ምስክር ለማድረግ በጊዜ ቅደምተከተል አልተፃፉም፣ አንዱ የዘለለውን ሌላው ጨምሮ ነው፣ አንዱ ዘይቤያዊ አነጋገር ተጠቅሞ ነው እያሉ በግልፅ የተቀመጠውን ቃል በአስታራቂ ማብራሪያ መመልከት የተቦጨቀን ሹራብ በሌላ ጨርቅ አክሞ ራሱ ነው እንደማለት አይደለም? ልብስ ካሉት ቡትቶም ይለበሳል ግን ተቦጭቆ የተሰፋ ደግሞ ወጥ ይሆናል? ይቀጥላል...
May 10, 2025*ye hawariyat sira lay yemiyaweraw 40 Ken ke enesu ga kekoye behuala maregun nw *Ye lukas wengel lay emahos menged lay sayawikut abruachew yiguaz ende neber nw *ye matiwos wengel yemiyaweraw setochu bemelaekt tenegruachew sihedu ezaw tegeltolachew le hawryat gelila endihedu ende tenagere hawaryatm gelila hedew ende tegeletelachew nw yeminagerew Minun ke minu nw ante ayayizek andu sitet nw minamn mitilew yanebebkewn yeteredakew aymeslegnm
May 10, 2025