አንድ ጥያቄ አለኝ፡ ምን ያህል የኮሌጅ ፍቅረኛሞች ከልብ ይዋደዳሉ? ወይስ ጊዜ ለማሳለፍ እና ብቸኛ ላለመሆን ሲሉ ነው የሚገቡበት? ምን ያህሉ ሰው ነው አሁን ፍቅረኛዬ ሆኖ ያለው ወንድ/ሴት የወደፊት ባሌ/ሚስቴ ነው ብሎ የሚያምነው? ደግሞ አንዳንዱን ሳይ፣ ግን ይሄ ነገር የሚዘልቅ ነው ያስብላል። ለምሳሌ:- አንዳንድ ጥንዶች ከሚራራቅ ሀገር የመጡ ናቸው፡ ሲመረቁ ወደየሀገራቸው እንደሚመለሱ ረስተውት ነው? -ሌላው ደግሞ ከተለያየ ሃይማኖት ናቸው። ይሄ ኢትዮጵያ ውስጥ የተለመደ ነው ግን ቀላል አይደለም። ምን ያህሉ ጥንድ ነው እንደነዚህ ዓይነት ሁኔታዎችን ገምግሞ እየተጠባበሰ ያለው? ወይስ ኮሌጅ አብረን እስከቆየን ድረስ አብረን ነን ከዛ በኋላ ግን የመጣው ይምጣ ነው።
4 votes