የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ ለሀገር እና ለህዝብ ያበረከተችው አስተዋፅዖ ምንድነው ? ያላችሁን ሀሳብ እና አስተያየት በቅንነት እና በስርዓት መልስሉኝ ። 1. የበአላት መብዛት ግን ትክክል ነው ብላችሁ ታስባላችሁ? 2. የቤተክርስቲያኗ መምህራን እና አባቶች የምንላቸው በተለይ በየከተማው ያሉት ለምእመናኑ በአሁኑ ሰዓት አርዓያ መሆን የሚችሉበት ሁኔታ ላይ ናቸው? 3. አክራሪ አማኝ የሚባሉትስ ለምን ፀባያቸው ከሰውኛ ፀባይ የወጣ ሆነ ? ማለት ወደ እግዚአብሔር በጣም መቅረብ ክፉ፣መሰሪ፣ቅናተኛ እና ተንኮለኛ ያረጋል ማለት ነው?
Sep 21, 20261.የበዓላት መብዛት ትክክል ነው ወይ አይደለም ስትል ሚያስማማን ምን common ground ኑሮ ነው ይሄን የጠየቅከው ሲጀመር አንተ ክርስቲያን አይደለህም። አጭሩ መልስ አዎ ለእኛ ትክክል ነው ላንተ ደግሞ አይመለከትህም። 2.አርአያ የሚሆኑ በጣም ብዙ ካህናት አሉ ጥቂት አርአያ ማይሆኑም ይኖራሉ ሆኖም ሁሉም በስራው ይጠየቃል እኛ ምንመራበት ቅዱስ ትውፊት አለን እንጂ በደመ ነፍስ ግለሰብ ተከታዮች አይደለንም። 3.ጥያቄው በእራሱ ጠማማ ነው። እንደ premise ያነሳኸው ሀሳብ በራሱ ሀሰተኛ ነው።ለስድብ እንዲመችህ ብለህ አማኝ አልካቸው እንጂ አይደሉም። የትኛው የቤተክርስቲያን አስተምህሮ ነው አንተ ያልካቸውን ነገሮች ሁኑ የሚለው? conclusionህ መሠረተ ቢስ የሆነ ስድብ ነው ይልቁንስ ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ማለት አንተ ካልከው በተቃራኒው ነው ቤተክርስቲያንም ምታዘን እንደዛ ነው።
Sep 22, 2026(edited)