ሰላም AAE's: በጣም የምወዳት ፍቅረኛ አለችኝ፡ እሷም ትወደኛለች ብዬ አስባለው፡ ባለፈው አመት ላይ relationship እንደጀመርን ወር ሊሆነን አካባቢ በስራ ምክንያት ችግር ውስጥ እንደገባች ነግራኝ ትልቅ ብር እንዳበድራት እና ስራው ሲስተካከል እንደምትመልስልኝ ጠይቃኝ እንደሌለኝ ነገርኳት፡ ከዛ ከሳምንት በኋላ ብሩን ማግኘት ባለመቻሏ ትልቅ ችግር ውስጥ እንዳለች እና ነገሮች እስከሚስተካከሉ ድረስ መገናኘት እንደማንችል ነግራኝ 8 ወር ተለያይተን ቆየን፡ በዚ ዓመት ከ4 ወር በፊት ስደውልላት ነገሮች እንደተስተካከሉ ነገረችኝ፣ ያኔ የተፈረውን ነገር በዝርዝር አስረዳችኝ እና በጊዜ ሂደትም ድጋሚ ፍቅር ውስጥ ገባን፡ አሁን ላይ ጥሩ ነገር ላይ ነው ያለነው፡ ግን አሁንም ያለችው የንግድ ሥራ ውስጥ ብር ሲያስፈልጋት ትጠይቀኛለች፡ ባለችው ቀን ትመልሳለች፡ guys እንደኔ ሃሳብ በእውነተኛ የፍቅር ህይወት ውስጥ ገንዘብ matter ሊያደርግ አይገባም፡ መደጋገፍ ግድ ነው፣ ግን መጀመሪያ ላይ የጠየቀችበት ሁኔታ እና ከዛ በኋላ አጠፋፏ አሁንም እረፍት ሊሰጠኝ አልቻለም፡ ያኔም እውነቷን ቢሆንስ እና የእውነት የእኔ ሰው ነው ብላ ቢሆንስ የጠየቀችኝ እላለው አንዳንዴ ደሞ እፈራለው፡ እውነት ለመናገር ገንዘብ ማጣቴ ሳይሆን እሷን ማጣቴ ነው የሚያስፈራኝ፡ guys በቁምነገር እና በቅንነት ምን ትመክሩኛላቹ? ተጨንቄያለው፣
May 02, 2025ለምን በግልፅ አትጠይቃትም ለምንድን ነበር የጠፋሽው የነበረውን ችግር እንዴት አለፍሽው በላት አሁን ላይ relationship ውስጥ ከሆናችሁ ይህንን መጠየቅ መብትህ ነው ሲቀጥል ደግሞ መጠየቅ እያለ ለምን ራስህን ሰላም ትነሳለህ ፍቅር ውስጥ ከሆናችሁ ምንም ነገር ቅር ሊልህ አይገባም
May 02, 2025