Guys beqa ሁሉም ነገር በ ፈጣሪ አንደሚሳካ አምናለው ነገር ግን በቃ ሲጨነቅ ምናምን ፈጣሪን አላስብም ስደሰት ብቻ ነው ለማመስገን ምፈልገው, የሆነ ነገር ስሆንልኝ ብቻ ነው ማስበው ጥልቅ ሀጥያት ዉስጥ ስወድቅ አላስበውም አሁም ጭልም ብሎብኛል ጌታን ምን ማድረግ እንዳለብኝ አላቅም ልሄድ እችላለው ወደ ላይ በዚ ከቀጠልኩ. የሄድኩበት ሁሉ የነካዉት ያናገርኩት ነገር ሁሉ negive ነገር ነው መልሱ, ሙሉ ዙርያየ መጥፎ ነገር አየሆነ ነው በህዎቴ በጣም ትልቅ ሀጥያት ከ 4 ዓመት በፊት ሰርቼ ነበር ንስሐ ትቼው ነበረ አሁን ግን ድጋሜ ተመለስኩበት 😰 ደከመኝ ለ እናቴና አባቴ ነበር ነገር ግን በህይዎት ኖሬ ከማቃጥላቸው ብዬ አስባለው . ብቻ ግራ ገባኝ በጣም አስተዋይ ልጅ ጎበዝ ልጅ ነበርኩኝ አሁን ግን ሁሉም ይንቀኛል ይቀልድብኛል እኔን እንደተላላኪ ያዩኛል ብቻ እኔ ላይ ምራቅ መጥፋት ብቻ ነው የቀራቸው ዉሻ ራሱ ከኔ በላይ ምያከብሩ ይመስለኛል በዙሪያዬ ያሉ ሰዎች. በዚ በኩል እንዴት ብዬ ገንዘብ ማግኘት እንዳለብኝ አጨነቃለው, በዚ በኩል HO 3rd year temari ነኝ ትምርቱ ያስጨንቀኛል በዚ በኩል እናቴ ያማታል እንዴት መታከም አለባት አያልኩኝ አጨነቃለው ምን እንደማደርግ ከየትኛው አንደምሆን ግራ ገባኝ ማርያምን 🥹🥹 አሁን አሁንማ እንደ አይምሮ በሽተኛ ብቻዬን ሁላ ማውራት ጀምርያለው,
Apr 29, 2025ያለህበት ጭንቀት የብዙዎቻችን መሰናክል ነው። U can't control everything, but y can control the reaction u give to the thing happening in ur life. በቅድሚያ ተረጋጋ። ከራስህ ጋር ታረቅ። ያንተ ጭንቀት ምንም ነገር መቀየር እንደማይችል ተረድተሃል። አሁን የሚያስፈልግህ መፍትሄ መፈለግ ነው። አንተ ስትኖር ነው ለእናትህም ሆነ ለምትወዳቸው ሰዎች መትረፍ የምትችለው። በሰዎች የምትናቀው እራስህን ስትጥል ነው። አመጋገብህን አስተካክል። ንፅህናህን ጠብቅ። በቂ እረፍት አድርግ። Social media ላይ አትጣድ ጭንቀትህን ያባብሰዋል። እራስህን ከማንም ጋር አታነፃፅር። እያለፍክበት ያለሀው ውጣ ውረድ የአብዘኻኛው ወጣት እጣ ፈንታ ነው። Sport ስራ አዕምሮህን ያረጋጋልካል። በዚህ ስብራት ላይ እያለህ የፍቅር ግንኙነት እንዳትጀምር። እራስህን ለማሻሻል አንብብ፣ጠይቅ። ገንዘብ የሚገኝባቸውን መንገዶች አማትር። እመነኝ አንተ ከጠነከርክ ሁሉም ያልፋል። ወደ ፈጣሪህ ተመለስ። ለመንጀልህ ማርታን ጠይቅ። እናትህን አላህ የጤናን ካባ ያልብሳቸው። ተስፋ ቆርጠህ ለናቁህ ሰዎች መደበሪያ እንዳትሆን። እራስህን ለማሻሻል በምታደርገው ጥረት ይሉኝታ የሚሉት አደገኛ ደዌ እንዳይጠናወትህ። Don't give a shit about what others think about u. Be crazy about solving ur financial problems. I hope u will win the struggle and adversity u are facing!
Apr 30, 2025