Guys let me ask u a question የዳግማዊ ትንሳኤ እለት ለምንድነው ሰው በቤተክርስቲያን እየተጋባ ያለው ብዙ ሰርግ ስላጋጠመኝ ነው?
Apr 27, 2025#ዳግም ትንሳኤ ዳግም ትንሣኤ ማለት ምን ማለት ነው? በዋናው ትንሣኤ ሳምንት የምትመጣዋ ዕለተ እሑድ "ዳግም ትንሣኤ" ተብላ ትዘከራለች፣ ጌታችን በትንሣኤው ዕለት ማታ በዝግ በር ገብቶ፣ በቅዱሳን ሐዋርያት መካከል ተገኝቶ "ሰላም ለሁላችሁ ይኹን" በማለት ትንሣኤውን ሲገልጽላቸው ሐዋርያው ቶማስ አልተገኘም ነበር፣ በኋላ ከሔደበት ሲመጣ ጌታችን እንደ ተነሣ እና እንደ ተገለጸላቸው ሐዋርያት በደስታ ሲነግሩት "በኋላ እናንተ 'አየን' ብላችሁ ልትመሰክሩ፣ ልታስተምሩ፣ እኔ ግን 'ሰምቼአለሁ' ብዬ ልመሰክር፣ ላስተምር አይኾንም እኔም ካላየሁ አላምንም " አለ ስለዚህም የሰውን ሁሉ ይልቁንም የመረጣቸው የወዳጆቹን የልብ ዐሳብ የሚያውቀው፣ ቸርነቱ ወሰን የሌለው የባሕርይ አምላክ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ልክ እንደ መጀመሪያው ትንሣኤ ዕለት አበው ሐዋርያት በተዘጋ ቤት በአንድነት ተሰባስበው እንዳሉ በሩን ሳይከፍት ገብቶ "ሰላም ለሁላችሁ ይኹን!" በማለት በመካከላቸው ቆመ፣ ቶማስንም "ያመንህ እንጂ ተጠራጣሪ አትሁን፣ እነሆ የተቸነከሩ እጆቼንና እግሮቼን፣ የተወጋ ጐኔንም ናና እይ" ብሎ አሳየው፡፡ እርሱም ምልክቱን በማየቱ፣ በመዳሰሱ ትንሣኤውንና አምላክነቱን እንደ ፍላጎቱ በመረዳቱ "ጌታዬ አምላኬ ብሎ መስክሮ የክርስቶስን ትንሣኤ አመነ የሳምንቷ ዕለተ ሰንበት፣ የትንሣኤው ምሥጢር ለሁለተኛ ጊዜ ለሐዋርያት የተገለጠበት ዕለት በመኾኑ የትንሣኤው ሳምንት እሑድ 'ዳግም ትንሣኤ' ተብሎ ይጠራል ይከበራል ዮሐ.20፥24-30 ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ በተነሳ በስምንተኛው ቀን በዕለተ እሁድ ደቀ መዛረሙርቱ አይሁድን ፈርተው በተሰበሰቡበት ዝግ ቤቶ "ሰላም ለእናንተ ይሁን "ብሎ ዳግም ስለ ተገለጠ ዳግማይ ትንሳኤ ተብሏል ። ሁለተኛ ለምን ተገለጠ? ለሐዋርያው ቶማስ ትንሳኤውን ለማሳመን፦ የጌታችን ትንሳኤ ቶማስ ስለ ተጠራጠረ ጌታችን ቶማስ በተገኘበት ዝግ ቤት ተገልጦ ለቶማስ ና ወደኔ የተቸነከረውን እጄና ጎኔን ዳስስ ብሎታል ። ቶማስም የተቸነከረው እጁን አይቶ የተወጋውን ጉኑን በእጁ ዳስሶ የጌታችን ትንሳኤ አምኗል፣ ሃገረ ስብከቱም በሕንድ ስለ ነበረ ተጋድሎውም የፈጸመው እንዲሁም ሰማዕትነት የተቀበለው በሕንድ ነው፣ ያቺ የጌታችንን ጎን የነካች (የዳሰሰች) እጅ ሳትበሰብስ ከታቦት ጋር በመንበሩ ላይ ተቀምጣለች፣ እስከ አሁን ድረስ የሕንድ ሊቀ ጳጳስ ሲሾም በዛች እጅ ተመርጦና ተባርኮ እንደሚሾም አንዳንድ ሊቃውንት ይናገራሉ። ሰንበትን ሊያጸናልን፦ የአይሁድ ሰንበት፣ እግዚአብሔር 22 ፍጥረታትን ፈጥሮ ያረፈባትና እረፉባት ብሎ ያዘዘን ሰንበት ቀዳም (ቅዳሜ) ናት፣ በሐዲስ ኪዳንም ጌታችን የተጸነሰባት፣ ከሙታን መካከል የተነሳባት፣ አንዲሁም ደግሞ ለማጽናት ሁለተኛ የተገለጠባት (ዳግማይ ትንሳኤ)፣ መንፈስ ቅዱስ የወረደባትና ሐዋርያት ከመጀመርያዋቹ ክርስቲያኖች ጋር በኅብረት ሆነው መንፈሳዊ ስራዋች የሚሰሩባት ቀን ዕለተ እሁድ ነበረች። ቤተ ክርስቲያናችን ለቅዳሜ ቀዳሚት ሰንበት ለእሁድ ደግሞ ሰንበተ ክርስቲያን እያለች ለሁለቱም ቀናት እኩል ታከብራቸዋለች ጌታችንም ይቺ ቀን እረፍትነቷን ለማጽናት ሁለተኛ የተገለጠባት ቀን ናት፣ እረፍት ስንልም ስራችንን ትተን ቁጭ ብለን (ተኝተን) የምናሳልፈው ማለት አይደለም፣ እንደውም ከማንም ቀን በላይ አብዝተን መንፈሳዊ ስራዎች የምንሰራባቸው ቀናት ናቸው። ምትሐት አለመሆኑ ለማስረዳት፦ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምትሐት እንዳልሆነና ቀድሞ የተዋሃደው ስጋና መለኮት፣ ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ መሆኑ ለማስረዳት ለሁለተኛ ጊዜ ተገልጦላቸዋል፣ በዝግ ቤት መግባቱ ደግሞ መለኮት እንዳልተለየውና ስጋ ብቻው እንዳልሆነ ለማስረዳት ነው ። "ሳያዩ የሚያምኑ ብጹአን ናቸው" ዮሐ.20፥29 አንድም ዳግም ማለት ሁለተኛ ማለት ነው፣ ጌታ ሁለት ጊዜ አልተነሳም፣ ዳግም የተባለው የትንሳኤው ስርዓት እና ቃለ እግዚአብሔር በዚህ ቀን ስለሚደገም ነው። 👉አንድም መነሳቱን ለ11ዱ ደቀመዛሙርት እንበለ ቶማስ ቢገልጥላቸው አምነው ለቶማስ ቢነግሩት የተቸነከሩ እግሮቹንና እጆቹን ካላየሁ ጣቴን በተወጋ ጎኑ ካላገባሁ አላምንም ብሎ ነበርና በሳምንቱ ያምን ዘንድ ቶማስ ባለበት ለሁለተኛ ጊዜ ተገለጠላቸው፡፡ ዮሐ.20፥26 እስከ ፍጻሜው 👉ቤተክርስቲያን ይህንን መገለጥ ዳግም ትንሳኤ ትለዋለች፡፡ ✍ፈጸምነ ይባላል፦ ይህ ስያሜ ደግሞ የፋሲካን በዓል አከበርን ስርዓቱን ዛሬ ፈጸምን ለማለት ነው፡፡ ✍አግብኦት ግብር ይባላል፦ በዮሐ 17፥ 1 ጀምሮ በተገለጠው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቃል መሠረት ጌታ " አባ ወአቡየ ግብረ ዘወሀብከኒ ፈጸምኩ " ያለውን መዘምራን በቅዳሴ ማጠቃለያ አካባቢ ስለሚዘምሩበት ነው፡፡ 👉ቶማስ ለምን ተጠራጠረ ? ✍መጠራጠሩ ስለ 2 ነገር ነው፦ 1.ሰዱቃዊ ስለነበረ ሰዱቃውያን ደግሞ ትንሳኤ ሙታን የለም ብለው የሚጠራጠሩ ናቸውና ሳላይ አላምንም ብሎ፤ 2.ሌሎች ሐዋርያት ትንሳኤውን ሲሰብኩ ተነስቶ አይተነዋል ሲሉ እርሱ ደግሞ መነሳቱን ሰምቻለሁ ብሎ ማስተማር ስለሌለበት ለማየት ሳላይ አላምንም አለ፡፡ 👉ጌታ የተገለጠላቸው ደጆች ተዘግተው ሳሉ ነበር ፡፡ ዮሐ.20፥26 ገብቶ ሰላም አላችሁ አስታረቅኋችሁ አላቸው፡፡
Apr 27, 2025