እስቲ ስለ እውነት እስቲ ማን ነው ትክክለኛው የአለም ቤዛ? ማነው ከነበረብን የሞት ፍርድ የተቤዠን? በእውነት ይሄን መመለስ ከብዶን ነው?
Apr 27, 2025ከነበረብን የሞት ፍርድ የተቤዠን እየሱስ ክርስቶስ ነው። ሌላ ማንም የለም። but when we use "ቤዛ" የሚለው ቃል without "ከነበረብን የሞት ፍርድ ያዳነን" ከሚለው ሀረግ ውጭ ስንጠቀም ለተለያዩ ነገሮች ክርስትያኖች ይጠቀሙታል። መጠቀም እንደሚቻል የእግዚአብሔር ሰዎች ሲጠቀሙት ስለተመለከትን ነው። “ኀጥእ የጻድቅ ቤዛ ነው፤ በደለኛም የቅን ሰው ቤዛ ነው።” — ምሳሌ 21፥18 እዚች ጋር ቤዛ የገባው ከሌላ ትርጉም ጋር ነው እንጂ ኅጥእ ጻድቅን ከነበረበት የሞት ፍርድ ያወጣዋል ማለት አይደለም። “ለሰው ነፍስ ቤዛው ሀብቱ ነው፤ ድሀ ግን ተግሣጽን አይሰማም።” — ምሳሌ 13፥8 ጌታ እየሱስ ብቻ ነው። ጌታ ከእየሱስ ጋር ሲመጣ ልዩ ትርጉም አለው። ግን መፅሀፍ ቅዱስ ላይ "ባርያው ጌታውን" or ጌታ የሚለው ቃል ለሰው ልጆች ሲጠቀም ከእየሱስ ክርስቶስ ጌትነት ጋር እንደማይገናኝ ልቦናችን ያውቀዋል። እኛ ክርስትያኖች ማርያምን ቤዛ ስንል የአለም አዳኝ እያልን እንዳልሆነ ልቦናችን ያውቀዋል። ለአለም ሁሉ ለሰው ልጆች ሁሉ ቤዛ የሆነው ከጨለማ ያወጣን ሀብት ሳይሆን ማርያም ወይም ፃድቃን ሳይሆኑ እየሱስ ክርስቶስ ነው። #እናውቃለን_አንደነግጥም
Apr 27, 2025