እንዴት ናችሁ በጣም ስለጨነቀኝ ነው አማክሩኝ እኔ ጋ በአደራ የተቀመጠ የሰው ብር ነበረ በአጋጣሚ ቤተሰብ ችግር ያጋጥመው እና እንከፍላለን ብለው 250,000 ብር አበደርኳቸው። እና ብሩን እስካሁን መመለስ አልቻልንም የብሩ ባለቤት ደግሞ ከቤተሰቦቹ በላይ አምኖኝ ነው እኔ ጋ ያስቀመጠው እና ምንም ነገር አያውቅም ። ከ 1 ወር በኋላ መጥቶ በገንዘቡ የሆነ ነገር ለማድረግ እንዳሰበ ነግሮኛል ለሱ ያለውን ሁኔታ ማስረዳት ምናምን ጭራሽ አይታሰብም።በመከራ ያገኘው ገንዘብ ነው እናት አባት የለውም። ቢያውቅ አዕምሮውን ሊስት ይችላል ቤተሰቦቼን እንዳልጠይቅ ደግሞ ከዚህ ገንዘብ ውጪ በጣም ብዙ እዳ ውስጥ ናቸው (700k ሚደርስ ብር እዳ አለባቸው) እባካችሁ መፍትሄ ካላቹ እርዱኝ በጣም ተጨንቀናል
Sep 01, 2026ለምን እን ደሆነ አላውቅም አንብቤው ስጨርስ ተናድጃለሁ። እንደዚህ አይደረግም አምኖህ አስቀምጦ። ወይም የነሱን ቶሎ የመመለስ አቅም ማገናዘብ ነበረብህ በቃ የአደራው ብር እንደሌለ ነበር ማሰብ የነበረብህ እንደማይነካ። ከየትም ተበዳድረህ መልስ ይሄ ያንተ ችግር ነው
Sep 02, 2026