Selam endet nachu Esti kene metberetu erdugn mekerugn dero haymanote lay tenkara neberku kehone gize behuala gen tefaw kesu menged wetche bezu hatyat lay wedeku anhun gen bektognal bezu yelefahubeten tesfayen Hulu yetalkubeten neger atechealew betam keftognal memeles efelegalew kesu menged wetche yetem endemalders teredchewalew endalemeles demo feraw Esti mekerugn ena demo setaznu tesfa setkortu metsemuachewen mezmuroch ye metshaf kedus teksoch lakulgn amesegnalew🙏
Apr 24, 2025ሮሜ 7:14-20 NASV [14] ሕጉ መንፈሳዊ እንደ ሆነ እናውቃለን፤ እኔ ግን ለኀጢአት እንደ ባሪያ የተሸጥሁ ሥጋዊ ነኝ። [15] የማደርገውን አላውቅም፤ ለማድረግ የምፈልገውን አላደርግም፤ ነገር ግን የምጠላውን ያን አደርጋለሁና። [16] ማድረግ የማልፈልገውን የማደርግ ከሆነ፣ ሕጉ በጎ እንደ ሆነ እመሰክራለሁ፤ [17] እንዲህ ከሆነ፣ ይህን የማደርገው እኔ ራሴ ሳልሆን፣ በእኔ ውስጥ የሚኖረው ኀጢአት ነው። [18] በእኔ፣ ማለትም ኀጢአተኛ በሆነው ተፈጥሮዬ ውስጥ ምንም በጎ ነገር እንደማይኖር ዐውቃለሁ፤ በጎ የሆነውን የማድረግ ምኞት አለኝ፤ ነገር ግን ልፈጽመው አልችልም። [19] የማደርገው ላደርገው የምፈልገውን በጎ ነገር አይደለም፤ ዳሩ ግን ለማድረግ የማልፈልገውን ክፉ ነገር ነው። [20] ላደርገው የማልፈልገውን ነገር የማደርገው ከሆነ፣ ያን የማደርገው እኔ ራሴ ሳልሆን፣ የሚያደርገው በእኔ ውስጥ የሚኖረው ኀጢአት ነው። አየህ ወንድሜ እኛ ብቻ አይደለንም ትልቁ ሐዋርያ ጳውሎስ እንኩአን በዚ ነገር ሲፈተን ነበር..... ግን ፈተናው ጋር ብቻ አላበቃም በተፈጥሮዬ ለሀጥያት ባርያ ነኝ ካለ በኃላ ምዕራፍ 8:1 ላይ እንዲ አለ ሮሜ 8:1-4 NASV [1] ስለዚህ በክርስቶስ ኢየሱስ ያሉት አሁን ኵነኔ የለባቸውም፤ [2] ምክንያቱም የሕይወት መንፈስ ሕግ በክርስቶስ ኢየሱስ ከኀጢአትና ከሞት ሕግ ነጻ አውጥቷችኋል። [3] ሕግ ከሥጋ ባሕርይ የተነሣ ደክሞ ሊፈጽም ያልቻለውን፣ እግዚአብሔር የገዛ ልጁን በኀጢአተኛ ሰው አምሳል፣ የኀጢአት መሥዋዕት እንዲሆን በመላክ ፈጸመው፤ በዚህም ኀጢአትን በሥጋ ኰነነ፤ [4] ይኸውም በሥጋ ሳይሆን በመንፈስ በምንመላለስ በእኛ፣ ሕጉ የሚጠይቀው ጽድቅ ሙሉ በሙሉ እንዲፈጸም ነው። "አሁን ኩነኔ የለባቸውም" ይሄንን ቃል ሁሌ አስበው devil ሊያስረሳን ሚፈልገው የትኛውንም bondage ሚያልፍ በውስጣችን እንዳለ ነው:: ስለዚህ ይሄን አውቀህ ጨክነቅ መፀለይ ጀምር መፅሐፍ አንብብ
Apr 25, 2025