ትላንት ጠዋት 22 ወደሚገኘው የመሬት ልማት ቢሮ ጉዳይ ለማስፈጸም መሄድ ነበረብኝ.በሃሳቤ አካውንቴ ውስጥ 100 ብር ስላለ በሱ እሄዳለሁ ብዬ አቅጄ ነበር. ግን ATM ስሞክር ምንም ብር አልነበረውም. ግራ ገብቶኝ ቦርሳዬን ስፈትሽ የተቀዳደዱ 20 ብር አገኘሁ. እስከ መገናኛ ድረስ በነበረኝ 20 ብር የቀረውን መንገድ በእግሬ ተጓዝኩ. የመሬት ልማት ቢሮ ደርሼ ጉዳዬን ጨረስኩ.ቀጥሎ ወደ ስራ ቦታዬ መሄድ ነበረብኝ ነገር ግን ለትራንስፖርት አልነበረኝም. ከማንም መበደርም አልችልም ነበር.ግራ ገብቶኝ ቁጭ ብዬ ብዙ አሰብኩ. በመጨረሻም አይኔን ጨፍኜ ታክሲ ውስጥ ለመግባትና ረዳቱን ብር የለኝም ለማለት ወሰንኩና ተነሳሁ. ነገር ግን ጥቂት እንደተራመድኩ መንገድ ላይ የወደቀ 200 ብር አገኘሁ. ምን ልላችሁ ፈልጌ ነው... ያ የገጠመኝ ነገር እንዲሁ እንዲሁ የመጣ አጋጣሚ ወይስ እኛ ባናየውም እየሚያየን አንድ ኃይል አለ?
Aug 25, 2026Yalkew ewnethn kehone. Yemiyay hayl kalhone lela mnm lihon aychlm eyayeh nw malet nw haQ aleh
Aug 25, 2026(edited)