ጥያቄ ይድረስ ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጭ አንቀበልም ለምትሉ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች እኔም በመጽሐፍ ቅዱስ ብቻ እንድትመልሱልኝ የምፈልጋቸው ጥያቄዎች አሉኝ። ጥያቄዎቼ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ናቸው ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጭ ስለማትቀበሉ ከመጽሐፍ ቅዱስ ምእራፍና ቁጥር እየጠቀሳችሁ እንደ ምትመልሱልኝ ተስፋ አለኝ። 1ኛ የማርያም እናትና አባት ማን ማን ይባላሉ? መቼም ካላበዳችሁ ከሰማይ ወረደች አትሉንም።እናት አባት አላት ግን ስማቸውን ብትነግሩን 2ኛ ጌታችንና አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከማርያም እንደ ተጸነሰ እንደ ተወለደ እንዲሁም በዮርዳኖስ እንደ ተጠመቀ በቀራንዮ እንደ ተሰቀለ እንደ ተነሣ እንዳረገ መንፈስ ቅዱስን ለሐዋርያት እንደ ላከ ታምናላችሁ፡ ምክንያቱም እነዚህ ሐሳቦች መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስላሉ። ነገር ግን እኔን ያልገባኝ ክርስቶስ በስንተኛው ዓመተ ዓለም ከእመቤታችን ተጸነሰ የተጸነሰበት ወሩስ የትኛው ወር ነው? መቼስ ተወለደ፥ በስንት አመቱ ተጠመቀ፣ ምን ቀንስ ተጠመቀ፡ ክርስቶስ በአይሁድ እጅ መቼ ታያዘ በስንት አመቱስ ተሰቀለ የተሰቀለበት ቀንስ ምን ቀን ነው? ወደ ሰማይስ ያረገው መቼ ነው? መንፈስ ቅዱስንስ ለሐዋርያት የሰደደላቸው መቼ ነው? እነዚህን ጥያቄዎች መልሱልኝና በክፍል ሁለት ጥያቄ እመለሳለሁ። ማሳሰቢያ የምትመልሱልኝ ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጭ ስለማትቀበሉ በመጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ነው።
Apr 24, 2025ይሄን ሁሉ ማወቅ በህይወታችን ላይ የሚጨምረውን አንድ ነገር ንገረኝና እነግርሃለሁ። ለምሳሌ ኢየሱስ ከትንሳኤ በኋላ 40 ቀን አስተምሩዋቸው እንዳረገ ይናገራል። ታድያ ወሩና ቀኑ ምን ያረጋል? ለድህነት ደግሞ bible ብቻውን መች አንሶ ነው?
Apr 24, 2025