ሰላም ከ 3 ዓመት በፊት አንድ ጥያቄ እዚሁ ላይ ጠይቄ ነበር,, በጣም የሆነች ሴት ወድጄ ነበር ጥሩ ቀረቤታ ላይ እያለን እኔ ለአንተ አልገባም ብላ ራቀችኝ ምናምን በጣም ልመልሳት ሞከርኩ እየቀረብኩ ስመጣ እየወደድኩህ ነው እና ያን ስለማልፈልግ ብላ ራቀችኝ ብቻ አድራሻዋን አጠፋችብኝ, በቃ ሌላ ሰው ስላላት ይሆናል ብዬ ተውኳት እኔም ከዛ በስራ ምክንያት ከዛ ቦታ ለ 3 ዓመታት ርቄ ነበር ግን በነዛ ጊዜ አንድም ሴት ማውራት መተዋወቅ ምናምን ደብሮኝ ነበር በሆኑ በአጋጣሚሆችም ይችን ሴት just normal ጓደኛዬ እንደሆነች ለእናቴ አስተዋውቄ ነበር still now ደህና ናት ትለኛለች, እናም እዚ ከመጣው በኋላ ትላንት ቅዳሜ ከሰፈር ጓደኞቼ ጋር club ገብቼ አገኘዋት በጣም ተቀይራለች በጣም ደነገጥኩ በቃ ራሷን አሳልፋ የምትሰጥ ሆና አገኘዋት እሷም ደነገጠች ነገር ግን ስራዋን ልጆች ሲነግሩኝ ይዣት ለመግባት ተስማማው ከሷ ጋር ግን በቃ ውስጤ አዘነ በጣም, ምን እንደገጠማት ስጠይቃት ምንም ልትነግረኝ ልትነግረኝ አልፈለገችም በቃ ለራሴ ላገባት ወሰንኩ ግን ዛሬ ጓደኛዬ አይሆንም አለኝ mother ይሄን ካወቁ አስበው አለኝ እኔ ግን ልቤ ድሮም አሁንም እሷ ጋር ነው ትላንት አብርያት ሳድር አቅፌ ከመተኛት ውጪ ለምንም ነገር አቅሙን አጣው ሰክራ ምናምን ነበር ዛሬ አግኝቻት ሳወራት ድሮ የምታውቀኝ አይደለውም ከኔ ራቅ እባክህ አለችኝ ምን ላድርግ በኔ ቦታ ብትሆኑ ምን ታደርጉ ነበር???
Aug 23, 2026ቀናት የለወጠው ማንነት ይዛ ስለሚሆን ተጠንቀቅ ፤ ነገር ግን እርሷም ውስጥ ያንተ አይነት ስሜት እንዳለ በሆነ መንገድ አረጋግጥ ሳታውቅ እና አልገባህም ብላ ከሆነ የማይቀየር ሰው የለም ቤተ-ክርስትያን ውሰዳት ንስሐ ትግባ ፣ ፀበል ትጠመቅ ትክክለኛው ሰአት ሲደርስ በቤተ-ክርስቲያን ተጋቡ ግን ትክክል የመለወጥ ስሜት ውስጧ መኖሩን እና መለወጧን እርግጠኛ ሁን ከምትነግርህ ውጪ ተግባሯንም እይ ቀለል ባለ ፈተናም ፈትናት!
Aug 24, 2026