ለኦርቶዶክሳውያን ብቻ ኢየሱስ ክርስቶስ ማርያም መግደላዊትን አትንኪኝ ላላት ማረጋገጫው ምንድነው ማለት ለምን እንደዛ አላት ከጀርባው ያለው ምስጢር ምንድን ነው
Apr 21, 2025፡፡ ሉቃ 24፡1 ሌሎች ሲሔዱ ማርያም መግደላዊት ግን የደረሰበትን ሳላውቅ አልሄድም ብላ ቆማ ታለቅስ ነበር ጌታችንም ከወደኋላዋ መጥቶ ‹‹ ምን ሆነሽ ታለቅሺያለሽ ›› አላት የአትክልት ጠባቂ መስሏት ‹‹ ጌታዬን አንተ ወስደኸው እንደሆነ ሽቱ እንድቀባው ያደረክበትን አሳየኝ ›› አለቸው ‹‹ ማርያም ›› ብሎ ስሟን ሲጠራት ጌታ መሆኑን አውቃ ‹‹ መምህር ሆይ›› ብላ እጅ ልትነሳው ስትቀርብ ‹‹ ገና ወደ አባቴ አላረኩምና አትንኪኝ ሄደሽ ለደቀመዛሙርቴ ተነሣ ብለሽ ንገሪያቸው ›› አላት ዮሐ 20፡17 ሄዳ አብሥራቸዋለች ጴጥሮስና ዮሐንስ እየሮጡ መጥው መግነዙን እንጂ እሱን አላገኙትም ‹‹ በእውነት ተነሥቷል ›› እያሉ ተመለሱ ፡፡ ሰውን ወዳጅ ኢየሱስ ክርስቶስ መግደላዊት ማርያምን አትንኪኝ ያላት ጠልቷት ወይም ተጸይፏት አይደለም ፡፡ ትንሣኤውን ከሰው ልጆች ቀድማ እንድታይ የፈቀደላት ስለወደዳት ነው ፡፡ ታዲያ ለምን አትንኪኝ አላት ; 1ኛ - 3 መዓልት 3 ሌሊት በከርሰ መቃብር አድሬ እነሣለው ብሎ የተናገረውን ስለረሳች ስለ እምነቷ ማነስ ሊገስጻት ፈልጎ ነው ፡፡ ለመላእክት ስለምን ታለቅሺያለሽ ሲላት ጌታዬን ወስደውታል አለች እንጂ ‹‹እንደተናገረው ተነሥቷል›› አላለችም ዮሐ 20፡11-13 2ኛ - በዛው ወደ ባህሪ አባቱ የሚያርግ መስሏት እግሩን ስማ ልትሰናበተው ነበር ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ግን የማርግበት ጊዜ ገናነውና ለመሰናበት ብለሽ አትንኪኝ ሲላት ነው 3ኛ -ሥርዓተ ክህነትን ሲመሠርት፡- ሴቶች ካህን መሆን ሥጋ ወደሙን መፈተት እንደማይችሉ ሥርዓት ሲሠራልን ነው:: ለዚህም ማረጋገጫ ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስን እንዲዳስሰው የፈቀደለት ሲሆን መግደላዊት ማርያምን ግን አትንኪኝ ነው ያላት ዮሐ 20፡26
Apr 22, 2025