#law
ሰላም ሰላም ቤተሰብ ስለ ኣንድ ነገር ልጠይቃችሁ ከሁለት ወር በፊት ኣንድ ጓደኛየ ከሁለት ልጆቹ እናት ጋር በሆነ ነገር ተጣልቶ እሷም ገንዘብ እንደወሰዳት ለፖሊስ ተናግራ ኣስያዘችዉ እና ከኣንድ ቀን በኃላ ተፀፅታ ለማስፈታታት ስትሄድ ያለ ዋስ ኣንለቀዉም ተብላ እሱም ለኔ ደዉሎ እንዲዋሰዉ ጠይቆኝ በ 20,000ብር በዋስ ተፈታ።ከዛ በኃላ ታርቀዉ ለ ሁለት ወር ኣብሮ ቆይተዋል ገንዘብም ለልጆቹ ሰጥቶታል። ከሁለት ወር በኃላ ግን እሱ ከትግራይ ወደ ኣዲስኣበባ ወጣ እና ኣሁን እሷ ደዉላ እንዳቀርበዉ ካልሆነ እኔ በፓሊስ እንደሚታሰር ነገረችኝ። እና ዋስ ለምን ያህል ግዜ ነዉ ተፈፃሚ ሚሆነዉ ? ከእስር በኃላ ኣብሮ ቆይተዋል እና እዉነት እኔ ነዉ ሚጠየቀዉ ኣብሮ ከቆዩ በኃላ? እና ደሞ ልጁ ኣሁን ከትግራይ ስለወጣ ምን ላድርግ? እባካችሁ ምክራችሁ ስጡኝ።🙏
Aug 08, 20261 engagements