ሰላም በማርያም የሆነ ነገር በሉኝ ምን መሰላችሁ ባጭሩ ስለ betting ነው እማወራህ ግን ለየት ይላል የኔ የሄን ነገር ካወኩት አንድ 4 ዓመት ሁኖኛል እስከ እዛ ድረስ በጣም አሪፍ ልጅ ማለት ለቤተሰብ ታዛዥ ሰፈር friend ጋር አሪፍ ነበርኩ ላይ በጣም አሪፍ ነበርኩ በቃ ነገ እበላለሁ እያልኩ ማለት classm, ተውኩት በደንምብ አላነብም ቤተሰብን እዋሻለሁ ከዛ በቃ ውጤት አልመጣም ይባስ ብሎ lecollegm የማያስገባ ውጤት መጣ በጣም ነው የደነገጥኩት ግን ይሄሁሉ የሱ ነገር ምክንያቱም እስከ ሰባት ሰዓት ነው ነው besoccer lay አፍጥጪ እምውለው እሚገርመው አሁን ላይ እኔ 22 አመቴ ነው በዛ በመጣልኝ ዉጤት technic እና ሙያ ተመረኩ አሁን ላይ ያንን ነገር አልተዉኩም ይባስ ብሎ telebirr5kብተበድሬ አሁን 13kደርሷል አለበኝ ማርያምን ለዚሁ ብዬ yetebederkut አሁንም ላይ በቤተሰብ ጥገኛ ነኝ ስራ አለኝ 4200 ብር ናት ደምዜ እመቤቴን ብድሬን በደሞዝ እከፍላለሁ ብዬ ሳስብ በሁላ በዚሁ እጨርሳለሁ አላቅም ሱስ አደለም ግን አንድ ቀን በልቼ እወጣለሁ ነው አሳቤ ግን የጅል ሃሳብ እንደሆነ አቃለሁ ምን እንደማረግ ግራ ገብቶኛል አንድ ቀን እግዚአብሔር ነው እምላቺ እራሴን ላጠፋ ሂጄ ነበር ግን አላቅም ላጠፋ የሄድኩበት ቦታ ስደርስ ለምን ብዬ ተመለስኩ አሁንግን ወስኛለው ምንም ማረግ አልቻልኩም yikrta😭😭 ቤተሰቦቼ
Apr 20, 2025ወዳጅ አለም ይህ መፍትሔ አይሆንም። የሰው ልጅ በምድር ሲኖር በጣም መጥፎ ዋጋ የሚያስከፍሉትን ስህተቶች ይሰራል። ዋናው ነገር ከስህተቱ መማርና ከወደቁበት መነሳት ነው እንጂ ፈተናውን ከወደቅክማ ሰይጣን አንድ ጥግ ይዞ አሸነፍኩ ብሎ ለራሱ እንዲያጨበጭብ እያደረግከው ነው። የሰው ልጅ ራሱን ለማጥፋት አልተፈጠረም። የሰው ልጅ ራሱን ከተለያዩ ፈተናዎች ጠብቆ ራሱን ለጥሩ ነገር እንዲያበቃ ነው የተፈጠረው። አታምነኝም ነገር ግን ባንተ ላይ እየሄደ ያለው ክፉ ጊዜ ያልፋል። ጥሩ ጸሐይ የምትሞቅበት አስደሳች ጊዜ ይመጣል። ይህ የሚሆነው የፈተና ጊዜያት ባንተ ላይ እንዲያልፉ ስትፈቅድ፣ በራስህ እጅ ራስህን ወደ ጥፋት ካልወሰድክ ብቻ ነው። የተፈጠሩ፣ የሚፈጠሩ ነገሮች ሁሉ ሊያጠነክሩህ፣ ሊያጎለብቱህ እንጂ ለሌላ አይመጡም። የዘመኑ ወንድ ለትንሽ ለትልቁ ራሱ ላይ መጥፎ ውሳኔ የመወሰን አባዜ ተጠናውቶታል። ታገስ ሐቢቢ! ሰው ሁሉ በደረሱበት ችግሮች እንዳንተ ተስፋ እየቆረጡ በነበር ዛሬም ቢሆን የድንጋዩ ዘመን ውስጥ ነበር የምንቀረው። አባትና እናትህ (በአባትም በእናት በኩል ያሉ አያቶችህ፣ ቅድመ አያቶችህ..... እስከ ላይኛው አያቶችህ ሁሉ) አንተ ያሳለፍካቸውን መጥፎ ጊዜያት በዘመናቸው አሳልፈው ነው አንተ ወዲህ የመጣኀው። እንጂማ አንዳቸው ራሳቸውን አጥፍተው ቢሆን አንተም ባልተፈጠርክ። ፈጣሪህ ካንተ ለምድር የሆነ ነገር እንድታበረክት ፈልጎ አምጥቶሃልና ያን አላማ ሳታሳካ፣ ፈጣሪ ያንተ ምድራዊ ድርሻ አብቅቷል ብሎ ወደ ራሱ እስካልወሰደህ ድረስ በትዕግስት ፈተናዎችን ስለማለፍ እያሰብክ ኑር። ይህን መጥፎ ሱስ በምን መልኩ አልፌው ለታናሾቼ መማሪያ እሆናለሁ ብለህ አስበህ፤ ከራስህ እና አትችልም ካሉህ ሰዎችና ስሜቶች ጋር እልህ ተጋብተህ ይህን ችግር ተሻገር። ይህች ምድር ተስፋ ለሚቆርጡ አትሆንም። ጠላትና ተስፋ መቁረጥን አሸንፈህ፤ ከችግሮችህና ከመጥፎው የቁማር ሱስ ተላቀህ ለምስጋና እዚሁ እንደምትመጣ እርግጠኛ ነኝ። ሰኞን በብሩህ ተስፋ፣ ወፈር ባለ ቆራጥነት እንድትጀምረው እመኝልሃለሁ። መልካም ሰኞ!
Apr 21, 2025