Guys በጣም ጭንቀት አያስቸገረኝ ነው የ ግቢ ተማሪ ነኝ ትምርቱ ከብዶኝ ሳይሆን በቃ ለምን አንደሆነ ዝም ብሎ እራስህን አጥፋ ማንም አይፈልግህም የሚል ስሜት ይሰማኛል. አንድ ዓመት ግቢ አቁዋርጨ ገዳም ለመግባት አስብያለው ግን ቤተሰብ ምን ይሉኛል አያልኩ አስባለው i don't know what to do. Guys ጭንቅ አለኝ ማርያምን ብዙ ሚያስጨንቀኝ ነገር በዛ 🥹🥹
Apr 20, 2025አይዞን ወንድማችን። ይህ ነገር ፍሬሽ እያለሁ ያጋጠመኝ ነገር ነው። ሲመስለኝ አብዛኛው ወንድ ተማሪ ላይ ይፈጠራል። አንደኛ የማታውቀው ሀገር ላይ ባይተዋርነቱ፤ ሁለተኛ ምናልባት የገንዘብ እጥረት፤ ሶስተኛ የምግብ መለወጡ፤ አራተኛ ከዶርም ልጆች ጋር በሙድ አለመጣጣሙ...ብቻ ምን አለፋህ ጊቢ ሁሉም ነገር ያስጠላል። እኔን ራሴን ከማጥፋት ወይም ትምህርቱን ከማቋረጥ የታደገኝ ብዬ እማስበው አንደኛ ማህበራት ላይ መሳተፌ ይመስለኛል። በ15 አንድ ቀን በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ የምንወያይበት የውይይት ቡድን ነበር። እዛ እየሄድን ቢያንስ የተወሰነ ተንፈስ ብለን እንመጣ ነበር። ሁለተኛ የኪነጥበብ ማህበር ውስጥ መግባቴ ብዙ እኔን የሚመስሉ ጓደኞችን እንዳፈራ ያገዘኝ ይመስለኛል። ሶስተኛ ጊቢ ጉባኤ መሳተፌ የአብነት ት/ት መማሬ። ስፖርት መስራቴ ከድብርቴና ከጭንቀቴ በተወሰነ መልኩም ቢሆን እንድወጣ ያገዘኝ ይመስለኛል። ብቻ በአጠቃላይ አእምሯችን ፕሮግረስ የሚፈልግ ይመስለኛል ያንን ነገር ደሞ ከላይ የጠቀስኩትን በማድረግ ማስታገስ የሚቻል ይመስለኛል። እኔ ጊቢ እያለሁ አሁን አንተ ያጋራኸንን ሐሳብ ለአንድ የተመረቀ ጓደኛዬ አጋርቼው የመለሰልኝ መልስ ይገርመኛል። "ይሄ ስሜት ካልተሰማህ ትክክለኛው መንገድ ላይ አይደለህም" ነው ያለኝ። እኔም የምልህ ይህንኑ ነው። ። "ይሄ ስሜት ካልተሰማህ ትክክለኛው መንገድ ላይ አይደለህም" 🙏🙏🙏🙏
Apr 20, 2025