Anonymous
#education#personal#society
ሰላም ለዚህ ግሩፕ አባላት፣ በኢትዮጵያ ውስጥ ሶሻል ኢንተርፕራይዝ ወይም NGO መስርታችሁ የምታውቁ ወይም በቅርብ የምታውቁት ሰው ካለ ስለ ምዝገባ ሂደቱ ልምዳችሁን እንድታካፍሉኝ ፈልጌ ነበር። በተለይ ደግሞ አዲስ ለሚመሰረቱና ገና መጀመሪያ ደረጃ (early stage) ላይ ላሉ ድርጅቶች ፈንድ (fund) ከሚያደርግ አካል እርዳታ ለማግኘት ስታመቻቹና ስትመሰረቱ የነበረው ሂደት እንዴት እንደነበር፣ ፈንዱን ለማግኘት ምን እንደረዳችሁና ያለፋችሁበትን መንገድ የበለጠ ሊያጋራኝ የሚችል ሰው ካለ ብታራዱኝ ደስ ይለኛል። የምዝገባ ሂደቱ እንዴት እንደነበር፣ ምን ያህል ጊዜ እንደሚወስድና የሚያስፈልጉ ሰነዶችን ጨምሮ መረጃው ያላችሁ ሰዎች ኮመንት ላይ ወይም በውስጥ መስመር ብትጽፉልኝ በጣም አመሰግናለሁ። ebakachu
Aug 06, 20260 engagements