ኢዚህ ቻናል ያስተዋልኩት አንድአንድ ሰዎች ስለ ክርስትና ጥያቄ ያነሱና ከዛ የምር መልሱን ሰምቶ ለመለወጥ ለመረዳት ሳይሆን ጀስት ፅንፍ በወጣ ማይንድ ሴታቸው እናንተ በቅንነት በምትመልሱት መልስ ላይ ሙድ ይዘው ለመቀለድ ይሞክራሉ ስለዚህ ጌታችን እዳለው "የልጆችን እንጀራ ይዞ ለቡችሎች መጣል አይገ፟ባ፟ም አለ።" ማቴ 15 ÷ 26 ለምን እኛ ሰምተናቸው ህይወትን የምናገኝባቸውን አስተምሮዎች ለምን እንደ አበደ ውሻ እዚም እዚያም እያለ ለሚለክፋቹ በምትሰጡትም ምላሽ ለሚያላግጥ ሰው ላይ አውጥታችሁ ትባክናላቹ? ሚማር ካለ ምናምን ትሉኝ ይሆና ግን መማር ሚፈልግ ሰው እዚ ማንነቱን ሳያሳውቅ በሆነች ስም የራሱን አካውንት ከፍቶ ሲንቦራጨቅ አይገኝም። ስለዚህ እባካችሁ እባካችሁ "በእግራቸው እንዳይረግጡት ተመልሰውም እንዳይነክሷችኹ የተቀደሰውን ለውሻዎች አትስጡ ዕንቍዎቻችኹንም በዕሪያዎች ፊት አትጣሉ።" ማቴ 7 ÷ 6።
Apr 20, 2025እኔ በበኩሌ ምጠይቀው ያላወቀውን አካል ለማንቃት ነው እኔ በነቃኃት ልክ ቢያንስ ከእኔ በቀደመ እድሜ ክልል እንዲባንን እና እኔ በተጓዝኩበት መንገድ ሳይሆን በተሻለ እና በተቀደሰ መንገድ እንዲመላለስ የተሻለ ሰው እንዲሆን ነው ሙከራዬ(ፕሮቮክ ሚያደርጋቸው አካላቶች አይጠፋም ግልፅ ነው ) ግን መሆኑ ግድ ነው:: በተለይ ደግሞ ከተሳታፊው ይልቅ ማይሳተፈው ብዙ አካል ብዙ እንዲያውቅ እንዲያሰላስል እንዲጠይቅ በውስጥ ረድቶታል ብዬ ውስጤ ይነግረኛል ስለዚህ ያልከው ከመጨነቅ ቢሆንም (ተጋደሉ ስለተባልን መጋደያችን ደግሞ ቃሉን መመስከር ብቻ ስለሆነ 🙏🏾🫡) እኔን ከተመለከተ መልዕክቱ በግልፅ ነው ምናገረው አላቆምም እንደውም ሌሎች እንዲቀላቀሉ ምክሬ ነው... ብቸኛው የመጣብንን ሁሉ መውጫ ፈጣሪያችን ነው (ስንቱ ወጣት 25 ሳይደርስ ረሱን ሚያጠፋበት ተስፋ መቁረጥ ሚሰበረው በዚህ ነው ብዬ አምናለሁ)🙏🏾 ይቅር በለኝ ወንድም አለም ካስከፋሁህ
Apr 20, 2025