ኢትዮጵያ ከብዙ አገሮች ጋር ተጣልታለች። ከዚህ በፊት መረዳት ያለባችሁ ነገር፣ ኢትዮጵያ ማለት በታሪክ እንደ ሕንድ፣ ቻይና እና ቱርክ ያሉ ኃያላን ሀገራት ያህል ኃይለኛ ነበረች። አሁን በዚህ ወቅት ደካማ ብንሆንም፣ እነሱም በአንድ ወቅት ደካማ ነበሩ፤ ከዚያ በኋላ ግን ተሻሽለው ወደ አሁኑ ደረጃ ደርሰዋል። ኢትዮጵያም አንድ ስትሆን ምን ያህል ኃይለኛ እንደሆነች ሁሉም ያውቃሉ። በእስልምናም ራሱላችን (ﷺ) "ወደ ሐበሻ ሂዱ" ማለታቸውም የሚያሳየው የኢትዮጵያን ታሪካዊ ክብር ነው። መረዳት ያለባችሁ ነገር፣ ኢትዮጵያን ማፍረስ የብዙዎች ምኞት ነው። እኛ የቀጠናው ስጋት ነን። ቻይና እንደ ሄደችበት መንገድ ብንሄድ ኖሮ፣ ዛሬ እንዲህ ባልደረስን ነበር። በአገራችን ላይ ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራትም ቅናት በግልጽ ይታያል። አዳሜ፣ ራሳችንን ተያይዘን ድህነትን፣ ዘረኝነትን እና ጦርነትን ካላስወገድን፣ በየቀኑ በውጭ ኃይሎች ተፅዕኖ ሀገራችን ትጎዳለች። በተጨማሪም ለችግራችን ትልቁ ጥፋት ፋኖ፣ ቄሮ ወይም ሌላ ስም በማውጣት እርስ በርስ መከፋፈላችን ነው። ይህ ደግሞ ለውጭ እንድንጋለጥ በስርዓት (system) የተሠራብን ነገር ነው ብዬ አስባለሁ። በዚህ ጉዳይ ላይ የማያውቅ ሰው ጠላት ተብሎ ዝም ከሚባል ይልቅ እውነታው ሊብራራ ይገባል። የእነዚህ ጠላቶች ዋና ዓላማ ማኒፑሌሽን (manipulation) በመጠቀም እርስ በእርስ እንድንጋጭ ማድረግ ነው። ይህም ከመጀመሪያው ጀምሮ የታቀደ እቅድ ነበር። አሁን ግን ብዙዎቻችን የምናደርገው በቲክቶክ ላይ መጨፈርና መዝናናት ብቻ ሆኗል። ወላሂ፣ ይህ በጣም ያሳዝናል። እናንተ በዚህ ጉዳይ ላይ ምን ትላላችሁ?
Aug 02, 2026Ere yematah ketena yeketket. We are peoples like the other side of the world nigga. Erasachenen eyekoleln new dhnetachenen yeresanew. Do u think bezi sat 1 ye chinese or middle east nigga citizen Ethiopia yetabatua mil? Mezb lematalel teblo politicians kedrownm yetsafutn atmen.. we are people like others aleke. Endi ketenadedku koyche neber.
Aug 03, 2026