https://t.me/askAnythingEthiopia/172492 Bezihgnaw Qn lay abzagnaw sew yadinal sil nber gn hayimanot sayihon kerestosm mamen bcha nw miyadnew adel?
Apr 19, 2025#በተጨማሪ ሃይማኖት ያድናል ስንል በመጀመሪያ ሃይማኖት እራሱ ምንድንነው?? ሃይማኖት ማለት እግዚአብሔር አምላክ ለሰው ልጆች እራሱን የገለጠበት ትምህርት(እምነት)ማለት ነው። ለምሳሌ፦በእኛ ቤተክርስቲያን ውስጥ -ምሥጢረ ሥላሴ -ነገረ ክርስቶስ -ነገረ ቤተክርስቲያን -ነገረ ድህነት ይህ ሃይማኖት ነው። ይህ ሃይማኖት የሚገለጠው የሚሰጠው ከእራሱ ከእግዚአብሔር ነው። “ወዳጆች ሆይ፥ ስለምንካፈለው ስለ መዳናችን ልጽፍላችሁ እጅግ ተግቼ ሳለሁ፥ #ለቅዱሳን_አንድ_ጊዜ_ፈጽሞ_ስለ_ተሰጠ_ሃይማኖት_እንድትጋደሉ እየመከርኋችሁ እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ ሆነብኝ።” — ይሁዳ 1፥3 አንድ ጊዜ ፈጽሞ የተሰጠ ሃይማኖት አለ የተሰጠውም ከእግዚአብሔር ከአምላካችን ነው አንድ ጊዜ ለተሰጠው ሃይማኖት ደግሞ ተጋደሉ ብሎ ይመክረናል።ቅዱስ ጳውሎስ “መልካሙን ገድል ተጋድዬአለሁ፥ ሩጫውን ጨርሼአለሁ፥ #ሃይማኖትን_ጠብቄአለሁ፤” — 2ኛ ጢሞቴዎስ 4፥7 ሃይማኖት የሚጠበቅና ለሃይማኖት መጋደል ግድ ነው ቅዱስ ጳውሎስ ከእግዚአብሔር ዘንድ የተገለጠው፣ትምህርት(ሃይማኖት) እስከመጨረሻው መፃናቱን ይነግረናል ከእውነታው እንዳልወጣ ጭምር ይነግረናል። ከሃይማኖት መውጣት ሞትን ያመጣል ምክንያቱም ከእግዚአብሔር መለየት ስለሆነ እግዚአብሔር ለሰው ልጅ የገለጠው ሃይማኖት(ትምህርት)ሰው አሜን ብሎ መቀበልና መጽናት ያስፈልጋል። #የመፅሐፍ ቅዱስ ማህበር ያሳተመው የመፅሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ገጽ 11 ሃይማኖት "የሃይማኖት መሠረት የሰው ምርምር ሳይሆን የእግዚአብሔር የራሱ በተፈጥሮና በመፅሐፍ ቅዱስ መገለጥ ነው።ለዚህም መገለጥ ሰው የሚሰጠው ተገቢ የሆነ የአፀፋ ምላሽ ማመንና መታዘዝ ነው"
Apr 19, 2025