ብዙ ወንዶች የሚያገቧት ሴት ድንግል እንድትሆን ይፈልጋሉ፤ አንዳንዶች ደግሞ የመጀመሪያ መስፈርታቸው ያደርጉታል። የሁሉም ሰው አቋም እንዲህ ቢሆን ኖሮ ሴቶች ሁሉ በንጽሕና መኖርን ለወደ ፊት ትዳራቸው መቃናት ሲሉ ይለማመዱት ነበር። ነገር ግን፡ 👉 ራሱ ድንግልናውን ያልጠበቀ ወንድ ድንግል ሴት እንዲያገኝ እንዴት ይመኛል? 👉 ካላገባት ሴት ጋር ምንጣፍ መጋራት በሰው ቤት መግባትና ከባለ ትዳር ሴት ጋር እንደ ማመንዘር ነው። ያላገባች መሆኗ ልዩነቱ ባሏን መቅደመህ ብቻ ነው። 👉 ዛሬ የሌላዋን ንጽሕና አሳንሰህ አጥፍተህ፣ ነገ ላንተ ንጹህ ሴት እንድትጠበቅልህ መጠበቅ እንዴት ይቻላል? አንተ ድንግል ሳትሆንና የብዙዎችን ሕግ አፍርሰህ ድንግል ሴት መፈለግህ አያስገርምም?
Jul 31, 2026ይሄን በሌላ መልኩ እንዲህ አሲቢው አንድ ሴት ደሀም ሆነች ሀብታም ደሀ ወንድ ማግባት አትፈልግም ። አለመፈለግ ብቻ ሳይሆን የመጀመሪያ መስፈርቷ ሀብታም ማግባት ነው ። ለምን ይሄን ፈለገች አንልማ?! ለምን ራሷ ሰርታ ያንን ህይወት አትገነባምም አንልም አይደል?! ምክንያቱም ሴት ሁሌም ፍቅር እና እንክብካቤ ፈላጊ ናት በዛውም ልክ ወንድ ልጅም ክብሩን ወዳጅ እና አጥብቆ ፈላጊ ነው እና እንዲህ ቢመኝ ምንም ሚያስገርም ነገር አይኖረውም ለማለት ያህል ነው !። ከዛ ደሞ ኣንድ ሴት ድንግል ላለ መሆኗ ተጠያቂ ልትሆን ምትችለው ራሷ እንጂ ድንግልናዋን የሰጠችው ሰው መሆን አለበት ብዬ አላስብም ይሄ የጋራ ስሜት ነው ።
Jul 31, 2026