Tenkir10
#other
ስለመጪው ፍልሰታ ጥያቄዎች አሉኝ ! ፩. በአንድ ( አርብ ነሃሴ ፩ ) የሌሊት ቅዳሴ ፣ ኪዳን ፥ ሰዓታት ፤ ማህሌት አለ ? ስንት ሰዐት ይጀምራል ፪. መዘጋጀት ያሉብኝ ነገሮችን ንገሩኝ
Jul 29, 20263 engagements
ስለመጪው ፍልሰታ ጥያቄዎች አሉኝ ! ፩. በአንድ ( አርብ ነሃሴ ፩ ) የሌሊት ቅዳሴ ፣ ኪዳን ፥ ሰዓታት ፤ ማህሌት አለ ? ስንት ሰዐት ይጀምራል ፪. መዘጋጀት ያሉብኝ ነገሮችን ንገሩኝ
Jul 29, 20261 የለሊት ቅዳሴ የሚባል የለም ፆም ላይ ቅዳሴ ከሰዓት ቡኋላ ነው ቅዳሜና እሁድ ጠዋት ይቀደሳል አገልጋይ ካልሆንክ ሰዓታት ላይ መገኘት አይጠበቅብክም 2 ንስሐ መግባት የጸሎት መጽሐፍት ማዘጋጀት
Jul 29, 2026አሁን ለፍልሰታ ማለት ነው ማህሌት ሰዕታት ከዛ ኪዳን ከዛ ቅዳሴ ነው ሚሆነው ወይስ ቅደም ተከተል አለው ሌላ ?
Jul 30, 2026ቤተክርስትያን 6 ሰዐት(ከለሊት) ይከፈታል...ከዛ ሰዐታት ይጀመራል....ተአምር ይነበባል...ከዛ ኪዳን ይደርሳል(ኪዳን የ ሰዐታት ማብቅያ ነው)...ቅዳሴ ከ ሰዐት ነው ....ቅዳሜ እና እሁድ ግን ሰዐታት ከተጨረሰ ቅዳሴ ይገባል....ማሕሌት ክብረ በዐል ሲኖር(13,16,እሁድ እና እንደ ቤተክርስትያኑ ያለዉ ታቦት ቀኑ ሲሆን).....ከዛ ንስሀ መግባት, መስገድ,ማስቀደስ,ቁርባን መቀበል,መፀለይ...ከዛ ቀስ በቀስ ሁሉም ራሱ እየተረዳሽ ይሄዳል...
Jul 30, 2026