ሰላም ሁላችሁም እንዴት ናችሁ? በሚቀጥለው ዓመት 24 ዓመቴን እሞላለሁ ሴት ነኝ እና ዘንድሮ ነው ከዩኒቨርሲቲ የተመረቅሁት ከተመረቅሁ ለ6–7 ወራት ያህል ሆኖኛል ስራ ጠፍ አሁን ደግሞ የnail እና የአይላሽ ሙያ እየተማርኩ ነው ቢያንስ ለጥቂት ወራት ተቀጥሬ ሰርቼ ልምድ ማግኘት እፈልጋለሁ ከዚያ በኋላ የራሴን ሥራ ለመጀመር አስባለሁ በጎንም እንደ like human መሸጥ ገቢ የሚያመጣልኝ ሌላ ሥራ መስራት እፈልጋለሁ ለምሳሌ የSHEIN ትዕዛዝ ሥራ ወይም ሌላ ንግድ መጀመር እፈልጋለሁ የፍቅር ጥያቄዎች ሲመጡ እኔ ግን ሁሉንም እየሸሸሁ ነዉ ምክንያቱም አሁን ትኩረቴ ራሴን መገንባት ሙያ መማር መስራት እና በራሴ መቆም ላይ ነው ቢያንስ አንድ ነገር በእጄ እስኪኖር ሕይወቴን በተወሰነ ደረጃ እስካረጋጋ ድረስ ትኩረቴን አልቀይርም ይህ ውሳኔዬ ትክክል ነው? ወይስ ተሳስቻለሁ? እና ደግሞ like human የት መረከብ እችላለሁ ምን ሌላ አትራፊ ነገር ልስራ ሀሳባችሁን ስጡኝ
Jul 25, 2026Well I really don't know if ur doing the right thing or not but if there are no guys u like or somewhat interesting person doesn't shows up why rush it. Build ur self for now but if someone light up a fire don't push it back. Life is interesting when u experience the unexpected rather than the planed. Don't forget to enjoy everything( every little thing).
Jul 25, 2026