ሰላም ሰዎች እንዴት ናችሁ? አንድ ነገር እንድታማክሩኝ ፈልጌ ነበር። ምን መሰላችሁ እኔ ሰንበት ተማሪ ነኝ። እና አሁን ለሚመጣው ጊዮርጊስ ንግስ ቤተክርስቲያን #ወረብ እናቀርባለን። ታድያ ማይክ ያዝ ተባልኩ እና በቃ ጭንቀት ውስጥ ነኝ። ምን መሰላችሁ መያዝ የማልፈልገው አንደኛ ስለምፈራ ነው ሰው ፊት ምናምን...ደግሞ ድምፄም ብዙ አይደለም። ደግሞ በሌላ በኩል ከእኛ ወረቡን ከተለማመድነው ውስጥ በደንብ የያዘው የለም። ስላችሁ በደንብ አይችሉትም። እኔ አብነትም ስለምማር አለ አይደል ቀረብ ስለምል ምናምን ብቻ በቃ.... በእናታችሁ ግራ ገብቶኛል የወረቡ ቅኝት ይሄ ነው እስቲ ስሙትና የምትሉትን አጋሩኝ። ያው 😁እንደማያምር አውቃለው ግን ባይሆን ለክፋ ይሰጣል ወይ? ማይክ ልያዝ አልያዝ የሚለውን ከእናንተ ልስማ
Apr 17, 2025ለምን የሚያለማምዱዋቹን አገልጋዮች አታሰማቸውም ማይሆን ከሆነ ሌላ ሰው እንዲፈልጉ ግን ብዙ መፍራት ያለብህ አይመስለኝም
Apr 17, 2025