ኢትዮጵያ ውስጥ መቅረት አለባቸው የምላቸውን አስተሳሰቦችን ከታች ፅፊያለሁ የቀረ ምትሉትን ጨምሩበትና እንማማርበት 1. አንዱን ለማሞገስ ስንፈልግ ሌላኛውን የማጣጣል አባዜ 2. ሰው ችግሩን ሲናገር ባንረዳውም ከመስማት ይልቅ የራሳችንን ችግር ተደርቦ ለመናገር መቸኮል 3. የተበደሩትን ብር አክብሮ አለመመለስ፤ መመለስ ከምንችለው ብር በላይም እያወቅን መበደር 4. በሁሉም ለመወደድ መሞከር፤ አንዱን ጓደኛህን መልሰህ ከሌላኛው ጓደኛህ ጋር ማማት 5. ስለሰው መጥፎውን እንጂ ጥሩ የማውራት ልምድ አለመኖር፤ ለጥሩ ነገር ትኩረት አለመስጠት 6. ያልተወለዱበትን አካባቢ ቋንቋ አክብረው ለመናገር የሚሞክሩ ሰዎችን ጥረታቸውን ከማድነቅ ይልቅ በአነጋገራቸው/በአክሰንታቸው ማላገጥን እንደ እርድና ማየት 7. ከሰው ስኬት ይልቅ በውድቀቱ መደሰት 8. መጨረሻው የማይታወቅ የማማረር እና ሁሌም ችግር የማውራት አባዜ
Apr 16, 2025Besew hiwot gebto mabukat ለወሬ ሟች መሆን ,jaludn ende susegna mayet mekret alebachew ✊
Apr 16, 2025