ትላንት ቁማር ሱስ እንዳለበት ምናምን የሚናገር ልጅ post አየሁ እዚህ ቻናል ለይ እና በጣም ገረመኝ። የሁላችንም ታሪክ አንድ ነው ማለት ነው? ኮሜንት እንኳን ሳነብ በቃ የሚለያየው መጠኑ እንጂ ሁሉም አንድአይነት ታሪክ። እኔማ ጉዴን ለማን ልንገረው እላለሁ። ሰዎች ህይወታቸውን ከኮቪድ በፊት እና በኋላ እያሉ ይናገራሉ እኔ ግን ከቁማር በፊት እና በኋላ ነው ታሪኬ። መቼ ነው normal የምሆነው? ህክምና አለው? ቢኖረውም ደግሞ እዳ የሚባል ሌላ ጣጣ😢 ምነው እግዚአብሔርን ሰምቼ ቢሆን እና betting የጀመርኩባት ቀን ሌላ ነገር ባደረኩ።
Apr 16, 2025እየውልህ ብሮዬ... እኔ ቤቲንግ መጫወት ከጀመርኩ ድፍን ሰባት ዓመት ሞላኝ... በታሪክ ተበድሬ ተጫውቼ አላውቅምም አላስበውምም :: አሁንም ድረስ አልፎ አልፎ ለመዝናናት ካልሆነ እንጀራ ይሆነኛል ብዬ ቤቲንግ አልጫወትም
Apr 16, 2025