የቀጠለ... ብቻ አሁን ላይ ሆኜ ሳየው ቁማር ሙሉ በሙሉ ማንነቴን ቀይሮታል ብዬ አስባለሁ። ያለፉት 4 አመታት በተለይ በእኔ ህይወት ውስጥ የተፈጠሩ 80% major events ከቁማር ጋር የተያያዙ ናቸው ብዬ ነው ማስበዉ። በነዚህ አመታት ውስጥ ሙሉ በሙሉ ከእዳ ነፃ የነበርኩባቸው ቀናት ምን አልባት ከ10 አይበልጡም። ገና ጠዋት ስነሳ መጀመርያ ትዝ የሚለኝ ያለብኝ በመቶ ሺዎች የሚቆጠር እዳ ስለሆነ በቃ ድጋሚ ሞክር ሞክር ይለኛል። እኔ እና ቁማር merge ያደረግንም ይመስለኛል አንድ አንዴ። ግን እዚህ channel ላይ ራሱ ሰዎች ገና betting ለመጀመር አስበው ጥያቄ ሲጠይቁ ምናምን እንዳታደርጉት ብዬ comment ለመስጠት የሚቀድመኝ የለም ብዙ ጊዜ። በቁማር ወይም በማንኛውም ሱስ ውስጥ ያሉ ወይም የነበሩ እና አሁን ነፃ የወጡ ሰዎች ሀሳብ share የሚደራረጉበት እና እርስ በርስ የምንደጋገፍበት group ቢኖር ብዬም እመኛለሁ። ሰሞኑን በቃ ሁሉም ነገር አስጠልቶኛል ነገር ግን በእግዚአብሔር አምናለው። i hope this is not my end ስላዳመጣችሁኝ አመሰግናለሁ👋
This is my story ቁማር የጀመርኩበት ቀን ትዝ ይለኛል። እስካሁን ምነው ያን ቀን ይህን ባልወሰንኩ እላለሁ። መጀመሪያ ያሸነፍኳት 4000 ብር እስካሁን ባርያ አድርጋ አስቀረችኝ። በጊዜው ተማሪ ስለነበርኩ ከትራንስፖርት ብር ስለሚተርፈኝ በትንሽ በ50 ወይም ግፋ ቢል በ100 ብጫወት ነበር። ቀስ በቀስ ግን መጠኑ እያደገ መጣ። ቤት መዋሸት ጀመርኩ... ብር ለማግኘት። 200, 300, 500 እያለ ቀጠለ። እንደ በፊቱ በ50 ብር ምናምን መጫወት የማሸነፍ ተስፋ አይሰጠኝም። የሌለብኝን ብድር የመጠየቅ ባህሪ አመጣው። እሱም ልክ እንደ ቁማሩ በትንሽ ብር ተጀመረ። 300 እና 400። ተጠራቅሞ 5000 ምናምን ሲደርስ በግዜው ደነገጥኩ። ግን ያው ከስንት አንዴ ስለማሸንፍ አንዳንዱን እከፍላለሁ። አሁን ግን ያኔ የተበደርኩትን ዞር ብዬ ሳየው ያስቀኛል። ምክንያቱም አሁን እዳዬ በመቶ ሺዎች ነው። ከአንድ ሰው 3 እና 4 ዙር ተበድርኩ። የtelebirr እማ አይነገር። የቤተሰብ ሲም ካርድ አልቀረኝም። እንደ እኔ የሆናችሁ ብዙ እንዳላችሁ አውቃለሁ። እንዴት ነው ነፃ የወጣችሁት? ይቀጥላል...