#Urgent ሰላም ቤተሰብ ሰሞኑን ወደ ሞያሌ ለንግድ ስራ ልሄድ ነበር እና ሞያሌ ውስጥ የምትኖሩ ስለ ሞያሌ አሁናዊ መረጃ እንድትሰጡኝ ነበር Please ሞያልያንስ እነዚህን 10 ጥያቄዎች በቅንነት መልሱልኝ🙏🙏🙏 1.በአሁኑ ሰዓት በሞያሌ (በኢትዮጵያም ሆነ በኬንያ በኩል) የኢንተርኔት እና የኔትወርክ ጥራት እንዴት ነው? 2.የጥሬ ገንዘብ (Cash) እጥረት አለ ወይስ የኬንያ ሽልንግም ሆነ የኢትዮጵያ ብር በቀላሉ ማግኘት ይቻላል? 3. አሁናዊ የኛ ብር በኬንያ ገንዘብ ከፍተኛ እና ዝቅተኛ ከስንት እስከ ስንት ነው የሚመነዘረው? 4.በአሁኑ ሰዓት የድንበር መሻገሪያ ኬላዎች ስንት ሰዓት ተከፍተው ስንት ሰዓት ይዘጋሉ? 5.በመታወቂያ ብቻ መሻገር ይቻላል ወይስ ፓስፖርት እና የክትባት ካርድ የግድ ይፈልጋሉ? ድንበር ላይ አዲስ አሰራር አለ? 6.በአሁኑ ሰዓት የአካባቢው የፀጥታና ደህንነት ሁኔታ እንዴት ነው? በሰላም ተንቀሳቅሶ ለመስራት አስተማማኝ ነው? 7. ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ንፁህ፣ አስተማማኝ መብራት፣ እና የውሃ አቅርቦት ያለው ጥሩ ሆቴል የትኛውን ትጠቁመኛለህ? በቀን ዋጋቸውስ ስንት አካባቢ ነው? 8.ለስራ እና ለእንቅስቃሴ ይበልጥ የተመቸ እና ደህንነቱ የተጠበቀው የትኛው ሰፈር ነው? (የኬንያው ሳይድ ወይስ የኢትዮጵያው? 9.በአሁኑ ጊዜ በአካባቢው የወባ ስጋት ወይም ሌላ የጤና ወረርሽኝ አለ? 10. ለንግድ እቃ ለመረከብ እና ትርፍ ለማግኘት የት አካባቢ የተሻለ ነው?
Jul 11, 2026