ጥያቄ ለፕሮቴስታንት.... ይህንን ጥያቄ ስትመልሱ በቅድሚያ ዲኖሚኔሽናችሁን(አምልኮ ምትፈጽሙበትን ቤት ስያሜ ጠቅሳችሁ ጀምሩ). ካለዛ መልሳችሁ ለእኔ ውድቅ ነው ግዜ ሰጥቼ አላየውም:: ጥያቄ.. 1. ጥምቀት ለድህነት እና ለሀጢያት ስርየት ብላችሁ ታምናላችሁ? 2. ስጋና ደሙ እውነተኛ ስጋና ደም ነው ብላችሁ ታምናላችሁ? 3. ክርስቶሎጂን (ሚስጥረ ስጋዌን ) አብራሩ 4. ትሪኒቲን(ቅድስት ስላሴን ) አብራሩ 5. እንድፕሮቴስታንት 5ቱን ብቻዋች( 5ቱን ሶላ አብራሩ) አውቃለው ረጅም ነው ለመግለፅ ግን ትራይ ዩር ቤስት.. የቀረውን በምልልስ እናደረጀዋለን::
Apr 13, 2025እሺ ባቅሜ ልሞክር እኔ ሙሉ ወንጌል ነኝ 1 አናምንም። 2 እውነተኛ ሳይሆን ምሳሌ ነው ብለን ነው ምናምነው(ይቅርታ ግን ይሄንን "መሰለኝ" ብለህ ያዝልኝ እርግጠኛ መልስ ከፈለክ ጊዜ ስጠኝ) 3 "ሚስጥረ ስጋዌ" ምን ለማለት እንደሆነ ባይገባኝም ልዩነቱን ትንሽ አራራከው የ Protestant እና የ Orthodox basic ልዩነት ድህነት በእምነት ወይስ በእምነት + ስራ የሚለው ነው። 4 ስለ ስላሴ ተመሳሳይ አስተምህሮ እንዳለን ነው ማውቀው ግን ትንሽ ለማለት ስላሴ አንድ አምላክ በ 3 ማንነት ነው። በዚ ጉዳይ ሌላውን(ከክርስትና ውጪ ያለን)ትነሽ ግራ እንዳናጋባ ከፈለክ በውስጥ ማውራት እንችላለን። 5 ሀ,መፅሐፍ ቅዱስ ብቻ። ይሄ በዋናነት የማይሳሳት መጽሀፍ ቅዱስ ብቻ እንደሆነ እና የበላይ እንደሆነ ለማሳየት ነው ለ, እምነት ብቻ። ይሄ ከላይ እንዳልኩት ዋናው ልዩነት ነው። “ነገር ግን ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን እንዲጸድቅ እንጂ በሕግ ሥራ እንዳይሆን አውቀን፥ ሥጋን የለበሰ ሁሉ በሕግ ሥራ ስለማይጸድቅ፥ እኛ ራሳችን በሕግ ሥራ ሳይሆን በክርስቶስ እምነት እንጸድቅ ዘንድ በክርስቶስ ኢየሱስ አምነናል።” — ገላትያ 2፥16 ሐ, ጸጋ ብቻ። ጸጋ ማለት ነጻ ስጦታ ነው። የዳነውም በነፃ ነው። መ, ክርስቶስ ብቻ። አስታራቂ እና በሰው እና በእግዚአብሔር መሀል መግባት የሚችለው ክርስቶስ ብቻ ነው ለሚለት ነው1ኛ ጢሞ 2:5 ሠ, ክብር ለእግዚአብሔር ብቻ። ስለ አምልኮ ብቻ ሳይሆን በምናረገው ነገር ሁሉ ክብር ለእግዚአብሔር ብቻ ማድረግ አለብን ለማለት ነው
Apr 14, 2025