ሰላም ቤተሰብ እንዴት ናችሁ አንድ ከአቅሜ በላይ የሆነ ነገር አለ ምንድን ነው እሱ በህይወት ተጎሳቆልኩ ከሰው አነስኩ ከጓደኛ ተነጠልኩ የትንንሽ ህፃናት መሳቂያ ሆንኩ ሰዎች ሲያዩኝ ይጠቋቆማሉ ምን ልበላችሁ አንዳንድ ሰው አሽሙር የሚናገር አለ አፈርኩ ተገለልኩ ቤተ ክርስቲያን እንኳን መሄድ ያስጠላኛል ታድያ እኔ እራሴን ባጠፋ ምንድን ነው ሀጢያቱ አንዳንዴ የተሰደብኩትን ሳስበው እስካሁን በህይወት መቆየቴ በጣም ይገርመኛል ብዙ ነገር ተብያለሁ ለብዙ ጊዜ ቤት ዘግቼ አልቅሻለሁ የተወለድኩበትን ቀን እረግማለሁ አሁን እያለቀስኩ ነው የምፅፈው ማንነቴን አጥቼ ከሰውነት ወጣሁ ይህ ሁሉ በምን ምክንያት መሰላችሁ በመልኬ ምክንያት ነው አፍንጫዬ በጣም ትልቅ ነው መልከ ጥፉ በመሆኔ ነው ቀለል ልታደርጉት ትችላላችሁ በጣም ከባድ ነው ስራ መስራት ትምህርት ቤት መሄድ አልቻልኩም ልጅነቴን ወጣትነቴን በአግባቡ ሳልጠቀምበት አንገቴን ደፍቼ ቀረሁ አሁን ግን ደከመኝ እግዚአብሔር አለ ነገ ሌላ ቀን እያልኩ እስካሁን አለሁ ግን በጣም ይደክማል የሰው አፍ አይን ቅስም ይሰብራል😭😭😭
Jun 30, 2026“ግሩምና ድንቅ ሆኜ ተፈጥሬአለሁና አመሰግንሃለሁ፤ ሥራህ ድንቅ ነው፥ ነፍሴም እጅግ ታውቀዋለች።” — መዝሙር 139፥14
Jun 30, 2026