ድሮ ወጣት እያለው ወደ እርሻ ስሄድ በዶሮዬ ላይ ተቀምጬ ሽምጥ እየጋለብኩ ነበር እና አንድ ቀን በ ሁለቱ ንቦቼ እርሻ ሳርስ ውዬ ቤት ስሄድ ውሀ የለም ውሀ አምጣ ተባልኩ በጣም በሽቄ ወደ ወንዝ ወረድኩ ወንዙ ግን ቀዝቅዞ በረዶ ሆኖ ነበር ከዛ በረዶውን ሰባብሬ በባልዲ አድርጌ ለመውሰድ ወሰንኩና ዞር ዞር ብዬ በረዶውን ምሰብርበት ድንጋይ ስፈልግ ድንጋይ አጣሁ ከዛ በጣም ተናድጄ ጭንቅላቴን ከአንገቴ ላይ ነቀልኩና በጭንቅላቴ በረዶውን ሰባብሬ ይዤ ስመለስ ሰዎች እኔን እያዩ ይገረማሉ ከዛ ምን ሆኜ ነው ብዬ መስታወቴን አውጥቼ ሳይ ለካ ጭንቅላቴ እዛ እረስቼው መጥቻለሁ። ይሄን ተረት መጨረሻው ምንድን ነው?..የሚያውቅ ካለ ነገሩኝ አመሰግናለሁ።
Apr 12, 2025Attention seeker hoe
Apr 12, 2025