ለረጅም ጊዜ ከራሴ ጋር በሙግት የቆየሁባትን። ምንም ትሁን የትም ትሁን ሠላም የምመኝላትን። ገና ሳያት ልቤ የሚርድላትን የምሳሳላትን። ነገ ነግቶልኝ የልጆቼ እናት እንድትሆን የምመኛትን። ምግባረ ሰናይ የሆነቸውን፣ ቅን አሳቢዋን፣ ታታሪዋን ሴት አገኘኋት። ቀርብኳት አገኘኋት አሁን ጊዜው ደረሰና ሩቅ ልትሔድ ነው። ስለዚህ ልነግራት ወሰንኩ። ምን ትመክሩኛላችሁ???
Apr 11, 2025እኔም እንደዛው ውስጥ ላይ ነኝ። የኔ እና የአንተ የሚለያየው እሷ አታቀኝም ከሰላምታ ውጭ። ጎረቤቴ ነች። የሚስት በሀሪ እንዳላት ፣ እኔ ብቻ አስደስቼያት እንደማኖራት ፣ ብቸኛ የሚወዳት ከልብ የሚፈልጋት ሰው እኔ መሆኔንም አረጋግጫለው። በቅርቡ ኢጣሊ ልትሄድ እንደሆነ ሰማው። ከምልህ በላይ ነው የምሳሳላት። አማራጭ ሆኜ ያገኘሁት። እንደ ምወዳት በብዙ መልኩ አሳይቻታለው። ብቻ እኔ ልመክርህ የምችለው። ካለመናገር ደጃዝማችነት ይቀራል ይባላል! ተናግሮ የመሸበት ማደርን የመሰለ ነገር የለም። ሰላም ሁን።
Apr 11, 2025