እባካችሁ ግራ የገባኝ ነገር ስላለ በጥሩ ምክር እርዱኝ። እኔ እና ፍቅረኛዬ ፍቅር ከጀመርን 6 አመት ሆኖናል። ነገር ግን እስካሁን ምንም አይነትsex አላደረግንም። ባለፉት 5 አመታት እኔ ራሴ ለሷ ካለኝ ክብር የተነሳ አልጠየቅኳትም ነበር። ከዩኒቨርስቲ ከተመረቅን በኋላ ግን አሁን ትክክለኛው ጊዜ ነው ብዬ በማሰብ ከ3 ወር በፊት ጠየቅኳት። ምላሽዋ ግን "አይሆንም" የሚል ነበር። እሷ ስለ ሴክስ ያላት አመለካከት ጥሩ አይደለም፤ እንደ መጥፎ ነገር ነው የምታየው። በተጨማሪም "አካሌን ከሰጠሁህ በኋላ ትተኸኝ ትሄዳለህ" ብላ በጣም ትፈራለች። እኔ ግን በጣም እወዳታለሁ፣ በፍጹም ልተዋት አልፈልግም። ወደፊት ከ3 አመት በኋላ ለመጋባት አስበናል፤ ነገር ግን ለ3 አመት ሙሉ ያለ ሴክስ መቆየት ለእኔ በጣም ከባድ ነው። እኔ እንደማንኛውም ትልቅ ሰው ፍቅራችንን ለማጠናከር እና ፍላጎቴን ከሷ ጋር ብቻ ለመወጣት ነው የምፈልገው። ከሌላ ሴት ጋር ሄጄ መዳራት አልፈልግም፣ እሷን ብቻ ነው የምፈልገው። እባካችሁ ምክር ስጡኝ። ያላትን ፍርሃት እንዴት ላስወግድላት እችላለሁ? እንዴትስ ላሳምናት እችላለሁ? እሷን ቀስ በቀስ ለማቅረብ የምጠቀምባቸው የፍቅር ቃላት፣ ሙዚቃዎች፣ ፊልሞች ወይም ማናቸውም ዘዴዎች ካሉ ጠቁሙኝ። አመሰግናለሁ።
Jun 25, 2026ለዝሙትማ አልተባበርም🤐
Jun 25, 2026