Aman_Y160
#sport
Gym ለመጀመር በቅድሚያ ምን ማወቅ አለብኝ ? ለምሳሌ ቶሎ ለውጥ ለማምጣት ? ሚገርመው አመጋገብ ላይ ዘመኔን ሁሉ በጣም አግበሰብስ ነበር አሁን ግን ስርአት መያዝ አለብህ ነው ያሉኝ እውነት ነው አ ? ወፍራምም ቀጭንም ሳልሆን መካከለኛ ነኝ ትንሽዬ ቦርጭም አለችብኝ። ልብስ ተውት ምንም ነው ማያምርብኝ። ስለዚ በ ሶስት ወር ውስጥ በትንሹም ቢሆን ለውጥ እና ቅርፅ ማየት እፈልጋለው። ግን በቃ አይገባኝም ጅም ገብቼ ማይሆነኝን ክብደት ከማነሳ እናንተ የምታቁ ሰዎች አመጋገቤን ጨምሮ ስለ ፕሮቲን ካርብስ ወዘተ ንገሩኝ። ሙሉ ቀን የሞሽን ዲዛይን ስራ ስለምሰራም ወገቤን በጣም ነው የሚያመኝ ሳስበው መፍትሄ ሆኖ ያገኘሁት ጅም መግባት ብቻ ነው። እስቲ ምን አገኛችሁበት? ምን አተረፋችሁበት? ፕራይቬሲ እንደተዳፈርኩ ይገባኛል ግን ከየት ወደየት እንደተለወጣችሁበት የሚያሳይ ፎቶ ልትልኩልኝ ትችላላቹህ? ቻትጂፒቲን እና መስለኔዎቹን ለመጠየቅ ሞክሬ ነበር ግን ምንም አልገባ አለኝ ብዙ ነገር ነው የሚተነትኑት።
Apr 08, 20252 engagements