please send me a review of the book ከአድማስ ባሻገር by bealu girma
Apr 07, 2025የጽሑፉ ዋና ገጸ በሃሪ አበራና ሉሊት እንዲሁም የአበራ ጓደኛ ሃይለማሪያም ነው፡፡ ከብዙ ውጣ ውረፍ በኋላ ሉሊትና አበራ በፍቅር ወደቁ፡፡ አበራ በጣም ስለሚወዳት በሉሊት እንቅስቃሴ ሁሉ ይቀና ነበር፡፡ አንድ ጠዋት ሉሊት ያለወትሯ ሽቶዋን ነስንሳ ወደ ስራ ስትሄድ እንዴት ዛሬ ሽቶ ተቀባች ብሎ የጠረጠረው አበራ ከደቂቃዎች በኀላ ስራ ቦታዋ ሊያረጋግጥ ተነስቶ ይሄዳል፡፡ ሉሊትና አለቃዋ ለስራ በመኪና አሁን እንደወጡ የሉሊት መስሪያ ቤት ሰራተኛ የመኪናዋን ሞዴል ሳይቀር ይነግረዋል፡፡ በዚህም አበራ በጥቆማ በምን ማፈላለግ ጀመረ! ወደ አንድ መናፈሻ ውስጥ የተባለውን አይነት መኪና ያያል በጣም ይናደድና የዚህ መኪና ባለቤት ማን እንደሆነ ብሎ ጠየቀ፤የሆቴሉ አስተናጋጅም እስከ አልጋ ቁጥሩ ይነግረዋል፡፡ አበራ በቀጥታ ሽጉጡን ይዞ ወደ ተባለው አልጋ ሄዶ መስኮቱን ከሰበረ በኋላ ይተኩሳል! የተኮሰባት ሴት ትሞታለች፡፡ በጣም የሚገርመው መረጃው ሁሉ ትክክል አልነበረም! ሉሊት ስራዋ ላይ ነበረች ሟቿ ሌላ ሴት ሆና ተገኘች፤አበራም ወይኒ ቤት ወረደ፤ቅናት!
Apr 08, 2025