ሰላም ለእናንተ እኔ ዩንቨርስቲ ከ2ኛ ከመት ጀምሬ ፍቅር ገባልኝ ውጤት ከ3:9 ወደ 3:65 ወርዶብኝ ተመረኩኝ። ከአፈቀርኳት ዘጠኝ አመት ሆነኝ አሁንም አፈቅራታለሁ ግን ልትሰማ አልቻለችም ከሷ በጣም ቆንጆዎች ሴቶች እቀራረብና ፍቅር ግን ልይዘኝ አልቻለም።አሁን ደግሞ እናቴ አግብተህ ልጂህን ማቀፍ እፈልጋለሁ ትላለች።ከዛች ውጭ ማፍቀር አልቻልኩም ስላትም ልትረዳኝ አልቻለችም።
Apr 06, 2025ታፈቅራታለህ አደል ? ልታገባት ከዛም ቆንጆ ህይወት መኖር ነው የምትፈልገው ከሷ ጋር ? ስለዚ መስዋዕት መክፈል አለብህ። እንዴት የሷ መሆን እንደምትችል አሳያት። ንፁ ሁን። ለመቀራረብም ሞክር። እሷ አንተን እያየችበት ያለበትን አንግል ለማወቅ ሞክር። የተሳሳተ አመለካከት ካላት እንደተሳሳተች በተግባር አሳያት። ወደድኩሽ አፈቀርኩሽ ምን ትርጉም አለው ለሴት ልጅ ? እሷ ወደድኩሽ የሚላትን አላጣችም። መውደዱን በተግባር የሚያሳያትን ነው የምትፈልገው። ግን እሄን ሁሉ የምነግርህ የቻልከውን እንድታደርግ እንጂ የሷን አንተን አለመፈለግ ፍላጎት እንድትጥስ አይደለም። ለምንድን ነው አንተ ጋር ያልፈለገችው? ምን አልባት በቂ መሰረታዊ ምክንያት ሊኖራት ይችላል። ስለዚ መፍትሄውን አንተ ታውቃለህ። ከአንተ ንግግር ብቻ ተንተርሶ መፍትሄ ማቅረብ ስለሚከብድ። ቢያንስ ንፁ ፍቅርህን አሳያት። ሚስትህ ልትሆን አደል የፈለከው? ስለዚ የተቻለህን አድርግ ( የሷን ፕራይቬሲ እና ርስፔክት በማክበር )
Apr 06, 2025