ኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ 2 ከቁጥር 13 ጀምሮ እስከ 15 #"ቃየንም እግዚአብሔርን አለው። ኃጥያቴ ልሸከማት የማልችላት ታላቅ ናት። እነሆ ዛሬ ከምድር ፊት አሳደድኸኝ፤ ከፊትህም እሰወራለሁ፤ በምድርም ላይ ኰብላይና ተቅበዝባዥ እሆናለሁ፤ የሚያገኘኝም ሁሉ ይገድለኛል። እግዚአብሔርም እርሱን አለው። እንግዲህ ቃየንን የገደለ ሁሉ ሰባት እጥፍ ይበቀልበታል። እግዚአብሔርም ቃየንን ያገኘው ሁሉ እንዳይገድለው ምልክት አደረገለት።"# ከዚህ ታሪክ ውስጥ ጥያቄ የሆነኝ ከነአዳም በፊት ሌላ ሰዎች በምድር ነበሩ? ከነበሩስ እነማን ናቸው? የማንስ ዘር ናቸው? ቃየንን እንዳይገድሉት ለምን ምልክት አስፈለገ? የሉም ካላቹ ታዲያ ቃየንን የትኛው ህዝብ እንዳይገለው ነው እግዚአብሔር ምልክት ያደረገለት? Note:-መልስ ካለ በፀባይ መልሱ....ሌላ ነገር አያስፈልግም!
Apr 03, 2025ሃይማኖታዊ መልሱን እርግጠጛ ባልሆንም ግን የኖሩትን ዘመን ብዛት ከ መጻፉ ስናየው ከ 9 ክ/ዘመን በላይ ነው። በዚ ሁሉ እድሜ ቆይታ፣ እንኳን እነሱ የጛ ቅድመ አያቶች ራሱ 15፤ 20 ይወልዱ ነበር። የተወለዱትም ሲያድጉ እንደዛው፣ ይሄንን የህዝብ ቁጥር እድገት በ600 ወይ 700 አመታት ብናሰላው በመቶ ሺዎች ሚቆጠር ህዝብ ብዛት እናገጛለን።
Apr 03, 2025