“የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ።” — ሮሜ 12፥2 ይህን አለም ላለመምሰል በአይምሯችሁ መታደስ ተለወጡ እያለ ነው። ህይወት እና እያንዳንዱ ድርጊት የሚመራው በሀሳብ ነው።ለመቀደስ ከድርጊትህ በፊት መለወጥ ያለብህ ነገር ሀሳብ ወይም አይምሮ ይባላል። ባጭሩ ሀሳብህን ለመለወጥ - የምታየውንና የምትሰማውን ምረጥ። - መፅሐፍ ቅዱስ አንብብ። circleህን የእግዚአብሔር ነገር፣መልካም የሆነ ነገር የሚወራበት አድርገው። ያኔ ይህን አለም ይመስል የነበረው አይምሮህ ይለወጣል። አንተም ሀሳብህን ነህና ትለወጣለህ። ከዚ ሁሉ በፊት ግን ኢየሱስን "የግልህ"አርገህ ማመን መቀበል ያስፈልጋል።
Apr 03, 2025