#religion
ሰላም ኦርቶደክሳውያን እለተ ሰንበቱ የተባረከ ይሁንላቹ🙏 "አቡነ ረዳዮስም ታላቅ ክቡር ንዑድ በሆነ ግርማቸው ጸጋን ተላብሰው በማይታዩ መላዕክት ታጅበው ከበእታቸው ወጡ። በመንገድም ሦስት ቀሳውስት ተገንኟቸው። በወንጌል ሰላምታም ተሳለሟቸው። ይኽንንም ባደረጒ ጊዜ አጽዋማታቸውን አስታጒለው ነበረና እሳት ከሰማይ ወድቃ በላቻቸው። አቡነ ረዳዮስም የሆነውን ባዩ ጊዜ ምህረት ይደረግላቸው ዘንድ ተግተው ጸለዩላቸው። በዙሪያቸውም በነበሩት የሀገሬው ሰዎች ሁሉ ፊት ነፍሳቸው ተመለሰች። የእሳቲቱም ጥላሸት ተወግዳላቸው ሰውነታቸው ፈጽማ ዳነች። ንስሐም ገብተው ቀሪ ዘመናቸውን እግዚአብሔር በአቡነ ረዳዮስ ልመና ያደረገላቸውን ታላቅ ገድል እየመሰከሩ ኖሩ። ሞትንም ሞተው በታላቅ ግርማ መንግሥተ ሰማያት ገቡ። አቡነ ረዳዮስንም በገነት ተገናኝተዋቸው እጅግ አመሰገኑ። ልመናቸው ረድኤታቸው ከቶ አይለየን ለዘለዓለሙ አሜን።" የእኚህን ቅዱስ ገድል መፅሃፍ ያላቹ ብትልኩልኝ? በረከታቸው ይደርባቹ❤️ አመሰግናለው🙏
Mar 30, 20251 engagements