አንዳንድ ሙስሊሞች እንደሚሉት ሰው ሁሉ ሲወለድ ሙስሊም ነበር ስለዚህ መሃመድን እንደ ነብይ መቀበል necessary condition አይደለም ማለት ነው ሙስሊም ለመባል?
Mar 29, 2025ሐሳብ ቁጥር አንድ "አንዳንድ ሙስሊሞች እንደሚሉት.."? አንዳንድ ሙስሊሞች አይደለም ያሉት። ውዱ ነቢያችን ሙሐመድ (ሰዐወ) ናቸው ያሉት። ሙስሊም ሆነህ ስትወለድ ወላጆችህ ከሁለት አንድ ስራ ይሰራሉ። 1 በዚያው እስልምናህ አጽንተው ስለእምነቱ እውቀትህን እያሰፉ ይሄዳሉ። 2 በአላህ የካደ ካፊር አድርገው ከኢስላም አውጥተው ያሳድጉሃል። ኢስላም የነቢያቶች ሁሉ መንገድ ነው። ሙሐመድ የነቢያት ሰንሰለቱ መቋጫ ናቸው። ኢስላም ላይ ስትኖር ሙሐመድን እንደ ነቢይ ካልተቀበልክ ከላይ የመጣውን ሰንሰለት እንዴት አንተ ትይዘዋለህ? ሙስሊም ሆነህ መወለድህ አላህ የሰጠህ ጸጋ ነው። ነገር ግን ያን ጸጋ እንዴት መጠበቅ እንዳለብህ ደግሞ እየተማርክ መሄድ አለብህ። ሙሐመድን እንደ ነቢይ ካልተቀበልክ አላህን ከካዱ ካፊሮች በምንም አልተለየህም፤ ከኢስላም ወጣህ ማለት ነው። ምክንያቱም ሙሐመድን መቀበል የኢስላም እምነት ላይ እንድትዘልቅ ስለሚያደርግህ። ቀኝ መንገድ ላይ ተገኝተህ ሳለ "ቀኝ መንገድ ላይ በመሆኔ የቀኙን መንገድ መሠረታዊ ጭብጥ ብተወው ወደ ግራ አልሄድም" የሚባል ሐሳብ የለም። ሙስሊም ሆነህ ከተወለድክ ኢስላም ውስጥ የተቀመጡ መርሆዎችን መከተል አለብህ። እነርሱን ለቀህ እስልምና የለም።
Mar 29, 2025