ሰላም! እስከዛሬ ስለፍቅር ብዙ ተወርቷል። ። ዛሬ ጥያቄ አለኝ። ሶስተኛ ዓመት የዩኒቨርስቲ ተማሪ ነኝ። ከመጀመሪያ አመት ሁለተኛ ሴሚስተር ጀምሮ ከአንዲት ልጅ ጋር ተቀራረብን። ቀስ በቀስ አብረን ብዙ ጊዜ ስናሳልፍ፣ አሳይመንት ስንሰራ የበለጠ ተቀራረብን ። ፍቅረኛ ኖሮኝ አያውቅም። ልጅቷን በጣም ወደድኳት። ያለ እሷ ንባብ አስጠላኝ። ትምህርቴ እንደይስተጓጎል ፈራሁ። አንድ ቀን እንደምወዳት ነገርኳት። ሳቀ አለችና አሁን የፍቅር ህይወት አልጀምርም አለችኝ። ከነገርኳት በኋላ ተረጋጋሁ። ቴሌግራም ማውራት አቆምን። ከአንድ አመት በኋላ ማውራት ጀመርን። ልቤ እንደድሮው ይወድዳታል። ሌላ ሴት ማየት አልፈልግም። ግን ከሷ ጋር በሰላም መኖር እፈልጋለሁ። በቅርቡ አባቷ ሞቱ። ገና አልሄድኩም። ትንሽ ፈራሁ። ምን ትመክሩኛላችሁ?
Mar 29, 2025ሂድ ከጎኗ ሁን ምን ትለኛለች ሳትል አፃናናት አለሁልሽ በላት ግን በፍፁም አሁን ላይ ስለ ግንኙነታቹህ እንዳታነሳ ምክንያቱም ግዜው አይድለም አሁን ትኩረትህ ጎዳቷን እንድትቀንስ ማድረግ እና ትምህርቷን እንድጨርስ ማድረግ በተመሳሳይም አንተም ለመጨረስ ሞክር ስሜትህን ተቆጣጠር
Mar 29, 2025