ሰላም ሰዎች እንዴት ናችሁ ይህ ጥያቄ ለኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ነው pls እምነቴን አውቀዋለው የምትሉ ብቻ መልሱልኝ ማለትም አንባቢዎች 👍 1,ለምንድነው ገዳማት ላይ አማኞች ሲሄዱ ቡና አትጠጡ የሚባሉት? 2,እግዚያብሄር መፅሀፍ ቁዱስ ላይ አትጠጡ ብሎ ያዘዘውስ የቱ ጋር ነው ? ያው እንደሚታወቀው አነቃቂ ንጥረነገር አለው ለጤናም ቆንጆ ነው መልሱልኝ እስኪ tnx
Mar 24, 20251. አንዳንድ እንደየ ገዳሙ የገዳም ልዩ ሥርዐቶች ይኖራሉ። ለምሳሌ ጠላ ተጠጥቶ በዚያው ቀን የማይገባባቸው ገዳማት አሉ። ከዚያ ገዳም ጠላ ጠጥቶ መግባት አይቻልም። ከዚያ ገዳም ጠላ መጠጣትም አይቻልም። ይህ ማለት ግን እንደ ክርስትና ጠላ አይጠጣም የሚል ድምዳሜ አያስይዝም። የዚያ የገዳሙ የተለየ ሥርዐት ነው። አንዳንድ ገዳማት ደግሞ ሴት የማይገባባቸው አሉ። ከዚያ ገዳም ምሳሌ ክብራን ገብርኤል ሴት አይገባም። ይህ ማለት ግን ሴት ልጅ ገዳም እንድትገባ አይፈቀድም የሚል ድምዳሜን አያስይዝም። ወንዶች የማይገቡባቸው የሴቶች ገዳማትም አሉ። ለምሳሌ ጣና እንጦንስ ገዳም ይህ ማለት ወንድ ልጅ ገዳም አይገባም የሚል እይታን አይሰጥም። ለተጠቃሹ ቦታ ብቻ የሚያገለግል ሥርዐት አለና። እንደ ጠቅላላው ግን ሴትም ወንድም ገዳም መግባት ይችላል። ስለዚህ ያ ገዳም ለምን ይሄን አለ ? ታሪኩ ምንድነው ? ብሎ መለየት ይገባል ሁሉም ገዳማት ይሄን አያዙም እንደየአካባቢው ሁኔታ እና ጥቂቶች ናቸው ደሞም እዛው ገዳም ላይ በቆየንበት ጊዜያት ውስጥ ይህን አታርጉ አሉ እንጂ ከነጭራሹ ቡና አትጠጡ አይደለም ያሉት እዛ ገዳም ውስጥ አታርጉ ያሉት የገዳሙ ሥርዓት ስለሆነ ነው 2. አላዘዘም የለም። (አስተውል የገዳሙ ሥርዓት ስለሆነ እዛ በምትቆይበት ሰዓት ይሄን አዘዙ እንጂ ከነጭራሹ አትጠጡ አይደለም ይህን ለምን እንዳሉ ደሞ እዛው የሄድክበት ገዳም መጠየቅ ይቻላል ይነግሩሃል እና ደሞ አንዳንድ ገዳማት እንጂ ሁሉም አይደሉም ምክንያት አለው ለምሳሌ የሆነ ገዳም ላይ ስልክ ይዞ መግባት ሊከለከል ይችላል ለምን ሲባል የገዳሙ ሥርዓት ሆኖ ምክንያት አለው ለጸጥታ/ለአርምሞ/ለሱባኤ እርጋታ ምናምን እንጂ ስልክ መጥፎ ነው ወይም ተከልክሏል መቼም አትጠቀሙ አያስብልም)
Mar 24, 2025