ሰለም....ለኦርቶዶክሳውያን ጥያቄ ከቻላቹህ እናንተ ካልቻላቹህ ደግሞ ሚያዉቅ ሰዉ ጠይቃቹህ መልሱልኝ. 1. ለእግዚአብሔር ቅርብ የሆኑ ሰውች ከባድ ችግር(ሞት) ላይ ሆነዉ ሲለምኑት ለምን አይደርስላቸዉም? 2. ቤተክርስቲያን ከተሳለምን በኋላ ለምንድን ነዉ ምንቀመጠዉ? ባንቀመጥስ? Thanks...Have a nice Sabbath😊
Mar 23, 20251. መጀመርያ ምን ብለው ነው የለመኑት ሚለውን ማወቅ ያስፈልጋል ሌላው ለእግዚአብሔር ቅርብ የሆኑ ሰዎች ሲጀመርም ወደ እግዚአብሔር መሄድ ነው ሚፈልጉት ሌላው የገጠማቸው ችግር እንዴት እና ለምን መጣ ሚለውን እነሱ ብቻ ነው ሚያውቁት ለፈተና፣በረከትን ሊያመጣላቸው፣ሊያስተምራቸው አይታወቅም የእግዚአብሔር እውቀት ነው እኛ ከሩቅ አይተን ሁኔታውን መገመት አንችልም ቅርብ የሆኑ ሰዎች ራሱ እግዚአብሔር ነው ሚያውቀው ሁሉን እንደጊዜው እንደ እንደ አቅሙ የሚሰጥ ነው እኛ ተመሳሳይ ልኬት ሊኖረን አይገባም 1ኛ ቆሮንቶስ 10 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹² ስለዚህ እንደ ቆመ የሚመስለው እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ። ¹³ ለሰው ሁሉ ከሚሆነው በቀር ምንም ፈተና አልደረሰባችሁም፤ ነገር ግን ከሚቻላችሁ መጠን ይልቅ ትፈተኑ ዘንድ የማይፈቅድ እግዚአብሔር የታመነ ነው፥ ትታገሡም ዘንድ እንድትችሉ ከፈተናው ጋር መውጫውን ደግሞ ያደርግላችኋል። 2. ከተሳለምን እና ከጸለይን በኋላ ትንሽ እንድንቀመጥ አባቶች ይመክራሉ ለቸኮለ እና ላልተመቸው ግዴታ ባይሆንም ስንሳለምም ትንሽ ነገር መጸለያችን አይቀርም ተያያዥ ናቸው እና ለምን አረፍ በሉ ተባለ ቢባል ጸሎት አድርሰን ቁጭ ምንልበት ምክንያት ከጸሎት በኋላ የሰራነው ሃጢያት ሚያስወግድ አምላክ አለን ሃጢያታችን እዚህ አራግፈነው እየሄድን ነው ለማለት ነው። በመንግሥተ ሰማያት ያለውን እያስታወስን ነው ምናርፈው። ቤተክርስትያን ስለሄድን አረፍን ለማለት ነው። አንድ ሰው ከፀለየ በኋላ ለትንሽ ደቂቃ ቁጭ ብሎ ማሰብ ፀሎታችንን እኛን የሚጠቀም የማይጠቅመን መሆኑን ከእግዚአብሔር ጋር ስንነጋገር እራሳችንን በጥሞና በመሆን እራሳችንን እንድናዳምጥ ነው። ሌላው የፀለይነው ፀሎት በተረጋጋ እና በአርምሞ ሆነን እግዚአብሔርን እንድናስብ ያደርገናል።
Mar 23, 2025