sorry to say this ግን ክርስቲያኖች ስትነገሩን የነበረውን የፍቅር አምላክ እግዚአብሔር መፅሓፍቅ ቅዱስ ላይ ብፈልገው አጣሁት ፣ በተቃራኒው ያገኘሁት ለህፃናት ፣ ለእንሰሳት ፣ለሴቶች እንኳን የማይራራውን ነው 💔... ወይስ ከእዚክ መፅሓፍ ቅዱስ ውጭ ሌላ መፅሓፍ አለ ሕፃናት ልጆችሽን እያነሣ በአለት ላይ የሚፈጠፍጣቸው የተባረከ ነው። (መዝሙረ ዳዊት 137:9)
Mar 22, 2025ወይ ጠይቅ ሳይገባህ ብዙ አፍ መክፈት አያዋጣም ቀስ ብለህ ይሄ ምን ማለት ነው ብለህ መጠየቅ ትችል ነበር ትርፍ ነገር ከምታወራ ሰሞኑን ግን ብዙ አወራቹ የጠየቃችሁ እየመሰላቻሁ አንተ ለማወቅ የጠየክ ባይሆንም ግን ለሌሎች መልስ ይሆን ዘንድ መጽሐፍ ቅዱስን ቀድሞ ስለ መጽሐፉ የገነባኸውን መጥፎ ነገር ለአስተሳሰብህ እንዲገጥምልህ አርገህ አታንብብ አውድ የለውም እንዴ ትርጉም የለውም እንዴ በቃ የአንዳንድ ሰው እውቀት ይሄ ነው ? መመርመር፣የተብራሩትን ነገሮችን ማንበብ እና ማየት፣በቅንነት መጠየቅ ቀርቶ ነው በዚህ ልክ መጻፍ ስለተቻለ ብቻ አንተ ስለመሰለህ ብቻ እንዲ ምትለው እናስብ እንጂ አንተ ተናገርኩ ምትለው ነገሮች ምን ያህል በሰው ሚዚን ውስጥ እንደቀለልክ ብታውቅ ይጸጽትህ ነበር ለማንኛውም አውዱን አንብቡትን ስለምን እንደሚያወራ ከዛ ሃሳቡ እንደዚህ ነው መጽሀፍ ቅዱስ ህጻናትን ድንጋይ ላይ ፈጥፍጡ አላለም በፍጹም ነቢዩ ቅዱስ ዳዊት በትሩፋን መከራ ተገብቶ ስለ እነርሱ ቁጭት በጻፈው ትንቢት ነው ይኼ ቃል ያለው ፣ ባቢሎን ቤተመቅደሱን አርክሰው ፣ የእስራኤልን ሴቶች ደፍረው ህጻናቶቻቸውን ገለው ፣ ግማሹን ማርከው እንደ አህያ እንደ ፈረስ እየገረፉ ወደ ባቢሎን ሲወስዱ ፣ የተረፉትን ደም አፍስሰዋል ። እስራኤል በባቢሎን የተረገጡት መረገጥና የደረሰባቸው መከራ እጅግ ጽኑዕ ነውና አንቺ ወራዳ የባቢሎን ልጅ ሆይ ስለተበቀልሽን የሚበቀልሽ የተመሰገነ ነው ፣ የኛን ህጻናት ደም በአለት ፈጥፍጠሽ እንደገደልሽ ያንቺንም ህጻናት እንደዚሁ የሚያደርጋቸው ይምጣ ብለው በሀዘናቸው በልቅሷቸው ውስጥ አስቀምጠዋል። የተባለውም አልቀረ የእስራኤል አምላክ ቀኑ ደርሶ ባቢሎንን በተፋረዳት ግዜ በፐርዢያ ቁጥጥር ገብታ ብዙ ግፍ ደርሶባታል ። ስለዚህ ይህ ስለ ባቢሎን የተነገረ ነው። እስራኤላውያን በባቢሎን መከራ ስለጸናባቸው የባቢሎንን ሰዎች እየረገሟቸው ነው። በምሥጢር አጋንንትን በመስቀል ተሰቅሎ የሚያጠፋ ክርስቶስ በባሕርይው ክቡር ነው ማለት ነው።
Mar 22, 2025