ዘማሪዎቻችን "ኢየሱስ ቦኪሜ/ቦኪሜ ነህ ክርስቶስ" ሲሉ ቦኪም ያው የቦታ ስም ነው የእግዚአብሔርም መልአክ ከጌልገላ ወደ ቦኪም ወጥቶ እንዲህ አለ፦ እኔ ከግብፅ አውጥቻችኋለሁ፥ ለአባቶቻችሁም ወደ ማልሁላቸው ምድር አግብቻችኋለሁ እኔም። ከእናንተ ጋር ያደረግሁትን ቃል ኪዳን ለዘላለም አላፈርስም፤ እናንተም መሠዊያቸውን አፍርሱ እንጂ በዚህች ምድር ከሚኖሩ ሰዎች ጋር ቃል ኪዳን አታድርጉ አልሁ። እናንተ ግን ቃሌን አልሰማችሁም፤ ይህንስ ለምን አደረጋችሁ ? ስለዚህም። ከፊታችሁ አላወጣቸውም፥ ነገር ግን ያስጨንቋችኋል፥ አማልክቶቻቸውም ወጥመድ ይሆኑባችኋል አልሁ። የእግዚአብሔርም መልአክ ይህን ቃል ለእስራኤል ልጆች ሁሉ በተናገረ ጊዜ ሕዝቡ ድምፃቸውን አንሥተው አለቀሱ። የዚያንም ስፍራ ስም ቦኪም ብለው ጠሩት በዚያም ለእግዚአብሔር ሠዉ» መሣ 2፤1-5 እና መሳፍንት ላይ እንደተጻፈው እስራኤላውያን በአንድ ወቅት ከጥፋት መንገዳቸው ለመመለስ እጅጉን ያለቀሱበትና ለእግዚአብሔርም የሠዉበት ሥፍራ ነው.. በዚህም ምክንያት ያንን ሥፍራ ቦኪም ብለው ጠርተውታል.. ቦኪም ማለት የሚያለቅሱ ወይም የማልቀሻ ሥፍራ ማለት ነው። ኢየሱስ ቦኪሜ ነህ ሲባል ሰው ወደ እርሱ ቀርቦ የሚያለቅስበት እውነትኛ ሥፍራ በኢየሱስ ፊት ስለሆነ ነው።
Mar 22, 2025