ስም ለመቀየር ምን ያስፈልጋል በዚ ስም ፖስፖርት አውጥቼበታለው እሱንስ እንዴት ላድርግ ቀይረው ይሰጡኛል?? ደሞ ስሜ ብሪቱ ሆኖ አይደለም እምነቴን ስለቀየርኩኝ ነው 😊🥰 አመሰግናለው
Mar 22, 2025ከሌላ እምነት ወደ ኢስላም መጥተሽ ከሆነ.. 1, ስምሽ ሀይማኖት አዘል ስም፣ ከኢስላም ጋር የሚጻረሩ ስሞች ጋር የሚገናኝ ስም እና ጥሩ ትርጉም የሌለው ስም (ምሳሌ፦ ዳምጠው፣ መሐሪ፣ ዘሩ ከአብ፣ ገብረ ምናምኖች፣ ወልደ ምናምኖች ያሉበት ...) ከሆነ መቀየር ይኖርብሻል። ከዚያ ውጭ ከሆነ (ምሳሌ፦ ሰላም፣ አበበች..) መቀየር አይጠበቅብሽም። መቀየር ከፈለግሽ ግን መብትሽ ነው። 2. እንደ ተባለው ስምሽ መቀየር ያለበት ከሆነ ደግሞ የፓስፖርቱ ጊዜ እስኪያበቃ ድረስ በዚያው ይቀጥልና አንቺ ደግሞ ለዚህ የሚያስፈልገውን ነገር ሁሉ አሟዪ። ስም የማስቀየር ሂደቱን በትክክል ባላውቅም ሀይስኩል ተማሪ ሳለሁ 10ኛ ክፍል ማትሪክ ልንፈተን አንድ ተማሪ ወደኛ ክላስ ለመምጣት ብሎ ስሙን እንዳስቀየረ አስታውሳለሁ። ፍርድ ቤት ሄዶ አስመስክሮ እንደተቀየረለት አውቃለሁ። ሙሉ መረጃ ባይሆንም ፍርድ ቤት መሄድ ሊጠበቅብሽ ይችላል። የረሳሁት ነገር ኖሮ ካስታወስኩ እጨምራለሁ። ሌሎችም የሚጠቅም መረጃ እንደሚሰጡሽ ተስፋ አደርጋለሁ።
Mar 22, 2025