ሰላም👋 አንድ ጥያቄ አለኝ። እስልምና የሰላም እምነት ነው ሲባል ብዙ ግዜ እንሰማለን። ታድያ ይህ እውነት ከሆነ ኢስላማዊ ሀገራት በምንላቸው እንደ ኢራን ባሉት ሀገራት ለምን ሰዉ የሰቀቀን ኑሮ ይበዛል? በነዚህ ሀገራት የሚኖሩ የክርስትና እምነት ተከታዮች ለምን ስደት እና መከራ ይበዛባቸዋል? ብዙ ኢትዮጵያን ወደ አውሮፓ፣አሜሪካ እና ሌሎች ሀገራት ሄደው ሲለወጡ አረብ ሀገራት የሚሄዱ ዜጎቻችን ግን ለምን ኢ-ሰብዓዊ ነገሮች ይደርስባቸዋል?
Mar 20, 2025ሰላምታህን ተቀበልኩና ወደ መልሴ.. በመጀመሪያ ደረጃ አንድ ነገር አለ። ኢራን የምትባል አገር ከሙስሊም አገራት ተርታ አትመደብም። ምክንያት? ኢስላም ላይ አሉ የተባሉ መሠረታዊ ህግጋቶችን የምትጥስ አገር ናት። ማስረጃ? ቲክቶክ ላይ ግባ እና search አድርግ። Irani Shia prayer vs Sunni Muslim prayer ብለህ ፈልግ። ግልጽ ልዩነቶችን ታገኛለህ። ነቢዩ ሙሐመድ (ሰዐወ) "አሰጋገዴን አይታችሁ ስገዱ" ባሉን መሠረት ነው ለ1400 አመታት እየሰግን እዚህ የደረስነው። አንድም ነገር ከዚያ መለየት አይፈቀድም። እነርሱ ግን ስሜታቸውን ተከተሉ። በተጨማሪም እነርሱ ከቀሪው ሙስሊም አለም የሚለዩባቸው ብዙ ነገሮች አሉ። The difference between Shia and Sunni Muslim ብለህ ስትፈልግ ታገኘዋለህ። ዋናው ነገር ደግሞ ሺዓዎች አብዛኞቹን የነቢዩ ሙሐመድን (ሰዐወ) ባልደረቦች (ሶሐቦች) የሚያነውሩና የሚረግሙ ናቸው። ከነቢዩ ጋር ሆነው መከራ የቀመሱትን ሰሐቦች፣ እርሳቸው እዚህ ምድር ላይ እያሉ በጀነት ያበሰሯቸውን ሰሐቦች፣ "ምርጡ ትውልድ በኔ ዘመን ያሉ ትውልዶች ናቸው። ከዚያም ቀጥሎ ያሉት፤ ከዚያም ቀጥሎ ያሉት ናቸው።" ብለው ያሞካሿቸውን ሰሐቦች የሚያነውሩ ናቸው። ለሺዓዎች በቀጥታ ከኢስላም ለመውጣት ይህ በቂ ነው። በተጨማሪም እነርሱ ዐሊይ'ን እንደ ነቢይ፣ አለፍ ሲልም እንደ አምላክ የሚቆጥሩ፣ የዐሊይ'ን ልጆችም እንደዚያው የሚያስቡ ናቸው። እኛ ሙስሊሞች ደግሞ እነዚህን ሰዎች እንደተቀረው ሰሐባ ነው የምናያቸው። በአላህ ማጋራትም ከኢስላም የሚያስወጣ ሺክር ነው። ከፍረዋል። ስለዚህ አይምታታብህ። ሌላው ለንጽጽር ያነሳሐው ሐሳብ የፎረሸ ነው። የትም አገር ብትሄድ ሰቀቀን አለ። የትም ብትሄድ አፋኝ አለ። ምነው የትራምፗ አሜሪካ አልታየችህም? ዜጎች ታፍሰው እንዲወጡ እየተደረገ አይደለም? ጓንታናሞ የማነው? አደገኛ አጥፊዎች የሚታሰሩባት ከመሆን ባለፈ ያለ ምንም ጥፋት ገብተው እድሜያቸውን ጨርሰው የሚወጡበት የዱኒያ ጀሀነም አይደለችም? ህዝብ ሁሉ ወደ ዐረብ አገራት በባህርም ጭምር የሚሰደደው አሪፍ ገንዘብ ስለሚከፈለው እንደሆነ ግልጽ ነው። ከነአሜሪካ ክፍያ ባልተናነሰ ጥሩ ገንዘብ የሚሰራው የሙስሊሞቹ አረብ አገራት እንጂ የክርስቲያን ደሴት በሆነችው ቅድስት ኢትዮጵያ (¡) አይደለም። ሌላው ሐሳብ ምን መሰለህ? ለምንድንነው የኛ ሰዎች እዚያ ሄደው የሚሰቃዩት? የሚል ሐሳብ ነው። የኛ ሰው እንደምታውቀው ከስርዓት ማፈንገጥ የሚወድ ህዝብ ነው። መጠጥ ክልክል ነው ሲባል አይሰማ፣ ዝሙት ክልክል ነው ሲባል እዚህ እንደለመደው መስሎት አይሰማ፣ ስርቆት ክልክል ነው ሲባል እጁ አያርፍ። በችግር ይወጣና ማን ይያዘኝ ይላል። በነዚህ ጋጠ ወጥ ሰዎች ምክንያት ለእንጀራው የወጣ ንጹህ ሰው አብሮ ገፈቱን ይቀምሳል። ስለዚህ "የኛ ሰውስ ምን አጥፍቶ ነው?" ማለት ያስፈልጋል። አውሮፓና አሜሪካ የሚለወጥ እንዳለ ሁሉ ህይወቱ የሚበላሸው ብዙ ነው። አሜሪካ የወንጀሎች ሁሉ መነሻ ቦታ እንደሆነች ላርዳህ። ሙሾ አውርድ። በአለማችን ብዙ ሴቶች የሚደፈሩት የት ነው? አሜሪካ! አንድ ቪድዮ ጌም እየተጫወተ የኖረ ወጠጤ ጎረምሳ እየተነሳ በየአመቱ 40,000 ሰው የሚረሽነው የት ነው? አሜሪካ! የቁማርተኞች መናገሻ የሆነችው ላስ ቬጋስ የት ነው ያለችው? አሜሪካ! በነሜክሲኮና ጎረቤቶቿ አቀባይነት የአደንዛዥ እጽ መናኸሪያ የሆነችው አገር ማንናት? አሜሪካ! አንዲት አገር ውስጥ ደግሞ ዝሙት፣ ቁማር፣ ግድያ ካለ ያቺ አገር ላይ በደል ይበልጥ የተንሰራፋ ይሆናል። ስለዚህ ጆሮህ ለይቶ አይስማ። አይንህም ለይቶ አይመልከት። ይህን የጠየቅከው በስሜታዊነት ሙስሊሙን ካሸማቀቀልኝ ብለህ ነው። At least you had to do your research. ለነገሩ አይንህ እየመረጠ የሚያነብ ከሆነ ሪሰርቹን ራሱ ስትሰራ ጣትህ እየለየ ነው የሚተይበው። ለማንኛውም ጥያቄህን መልሻለሁ። ጨረስኩ።
Mar 20, 2025