ሰላም እንዴት ናችሁ ተወዳጆች ሁለት ጥያቄ ነበረኝ ለእስላሞች 1, ሁሌ ክርስቲያኖችን "ኢየሱስ ጌታ ነኝ" አላለም በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ሐዋርያቶቹ ነው እንደዛ ያሉት ትላላችሁ። ይህ የሐሰት ክስ ቢሆንም ቁርአናቹ ላይ አንድም ጊዜ አላህ ለመሐመድ ቀጥታ "አምላክ ነኝ" ያለበት ቦታ የለም። አምላክ ነኝ ያለው በጅብሪል በኩል ነው። እና እናንተ አምላክ የምትሉት እንኳን አምላክ ነኝ ያለው በመልእክተኛ በኩል ከሆነ ለምን ሐዋርያትንም አትቀበሉም? 2, በሐዲሳቹ ላይ መሐመድ የወንድ ልጅ ብልት ሲስም ሲጎትት እንደነበር ይናገራል። እና ግብረሰዶማዊያን ይህን ነገር አንስተው የሱን መንገድ ነው የምንከተለው ቢሏቹ ምን መልስ ይኖራቹሀል?
Mar 19, 2025ወደ መልሱ! ጽሑፎችህ በሙሉ በ wrong argument የተሞሉ ናቸው። አንድ በአንድ እንመልከታቸው። ከታች ኮሜንቶችህን አንብቤያለሁ። ጠያቂዎቹ ክርስቲያኖችን ግራ ለማጋባት ስለጠየቁ አንተም ግራ ለማጋባት ነው የጠየቅከው። እና ደግሞ እነርሱ እስካላቆሙ ድረስ አንተ መጠየቅህን ትቀጥላለህ።😄 በርታልን! መሆን የነበረበት አንተ ለማወቅ መጠየቅ እንጂ እነርሱ ስለጠየቁ መጠየቅ አልነበረም። ምነው ሰው ያልገባውን መጠየቅ አይችልም? አንተ መመለስ ባትችል መመለስ የሚችሉ አሉ። መመለስ የሚችሉ ባይኖሩ እንኳ መልስ የለውም ማለት አይደለም። ስለዚህ ረጋ በል እሺ ሐቪቪ። 20:14 إِنَّنِي أَنَا اللَّهُ لَا إِلَٰهَ إِلَّا أَنَا فَاعْبُدْنِي وَأَقِمِ الصَّلَاةَ لِذِكْرِي «እኔ አላህ እኔ ነኝ ያለ እኔ አምላክ የለምና ተገዛኝ፡፡ ሶላትንም (በእርሷ) እኔን ለማውሳት ስገድ፡፡ 51:56 وَمَا خَلَقْتُ الْجِنَّ وَالْإِنسَ إِلَّا لِيَعْبُدُونِ ጋኔንንና ሰውንም ሊግገዙኝ እንጅ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም፡፡ 53:62 فَاسْجُدُوا لِلَّهِ وَاعْبُدُوا ۩ ለአላህም ስገዱ ተገዙትም፡፡ 4:36 ۞ وَاعْبُدُوا اللَّهَ وَلَا تُشْرِكُوا بِهِ شَيْئًا ۖ وَبِالْوَالِدَيْنِ إِحْسَانًا وَبِذِي الْقُرْبَىٰ وَالْيَتَامَىٰ وَالْمَسَاكِينِ وَالْجَارِ ذِي الْقُرْبَىٰ وَالْجَارِ الْجُنُبِ وَالصَّاحِبِ بِالْجَنبِ وَابْنِ السَّبِيلِ وَمَا مَلَكَتْ أَيْمَانُكُمْ ۗ إِنَّ اللَّهَ لَا يُحِبُّ مَن كَانَ مُخْتَالًا فَخُورًا አላህንም ተገዙ፡፡ በእርሱም ምንንም አታጋሩ፡፡ በወላጆችና በቅርብ ዝምድና ባለቤትም፣ በየቲሞችም፣ በምስኪኖችም፣ በቅርብ ጎረቤትም፣ በሩቅ ጎረቤትም፣ በጎን ባልደረባም፣ በመንገደኛም፣ እጆቻችሁም ንብረት ባደረጓቸው (ባሮች)፣ መልካምን (ሥሩ)፤ አላህ ኩራተኛ ጉረኛ የኾነን ሰው አይወድም፡፡ 22:77 يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا ارْكَعُوا وَاسْجُدُوا وَاعْبُدُوا رَبَّكُمْ وَافْعَلُوا الْخَيْرَ لَعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ ۩ እናንተ ያመናችሁ ሰዎች ሆይ! (በስግደታችሁ) አጎንብሱ፣ በግንባራችሁም ተደፉ፣ ጌታችሁንም ተገዙ፣ በጎንም ነገር ሥሩ፣ ልትድኑ ይከጀልላችኋልና፡፡ 15:99 وَاعْبُدْ رَبَّكَ حَتَّىٰ يَأْتِيَكَ الْيَقِينُ እውነቱም (ሞት) እስኪመጣህ ድረስ ጌታህን ተገዛ፡፡ ከላይ የጠቀስኩልህ አንቀጾች አላህ በቀጥታ ሙሐመድንም ሆነ ህዝቦቹን እንዲገዙት ያዘዘበት አንቀጾች ናቸው። በጅብሪል በኩል? ቁርአኑ በሙሉ ከአላህ የተወረደው በጅብሪል (ዐሰ) አማካኝነት ነው። ታማኙ ጅብሪል ደግሞ ለሙሐመድ,(ሰዐወ) ብቻ ሳይሆን ለሁሉም ነቢያት መልዕክት አድራሽ ነበር። በጅብሪል ካልወረደ ከሰይጣን ይውረድልህ? ወይስ እንደናንተው ከኢየሱስ ውልደትና እርገት በምዕተ አመት ርቀት ላይ የሆነ ሰው ይጻፍልህ። የኛ ጥያቄ መጽሐፋችሁ መበረዙ እንዳለ ሆኖ እንኳ ቃል በቃል ጌታ ነኝ ያለበትን አስነብቡን ነው። ምክንያቱም አብ በግልጽ ጌትነቱን እንዳወጀ ወልድ በአንድም ቦታ አልተናገረም! የኛን ከናንተ አታደባልቅ። አታምታታ! በዚያ ላይ የናንተው የሚበላ፣ የሚጠጣ እና የሚጸዳዳ፣ የሚያንቀላፋ እና ሰው ላይ ያሉ ጉድለቶች የሚታዩበት ነው። የኛው አላህ ደግሞ ከቶ ያየውም የለም። የሰውን ልግ ከሚጎበኙት ጉድለቶች ሁሉ የጠራ ነው። 2 ሙሐመድ የወንድ ልጅ ብልት ሲስም ላልከው ማስረጃውን አስቀምጠህ ብትወያይ መልካም ነበር። ነገር ግን ይህ ሐዲሥ ደካማ እና ተቀባይነት የሌለው ውድቅ ሐዲስ ነው። ውድቅ የተደረገን ሐዲሥ ደግሞ ለማስረጃ ማቅረብ አይቻልም። አላህ የሉጥን ህዝቦች በስራቸው እንዴት እንደቀጣ ማስረጃችን 15:74 فَجَعَلْنَا عَالِيَهَا سَافِلَهَا وَأَمْطَرْنَا عَلَيْهِمْ حِجَارَةً مِّن سِجِّيلٍ ላይዋንም ከታችዋ አደረግን፡፡ በእነሱም ላይ የሸክላ ደንጊያዎችን አዘነብንባቸው፡፡ የሉጥን ህዝቦች የሸክላ ድንጋይ እያዘነበ ከላይ ወደ ታች ገልብጦ ነው ያጠፋቸው። ላንተም ለግብረሰዶማዊያንም በቂ መልስ ነው። ጥያቄዎችህ ተመልሰዋል። ጨረስን።
Mar 19, 2025